ሴዴቅያስ፥ ታማኝ እንዲሆንለት በእግዚአብሔር ስም ባስማለው በንጉሥ ናቡከደነፆር ላይ ዐመፀ፤ ተጸጽቶ ንስሓ በመግባት ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ በእልኸኛነት እምቢ አለ።
ኤርምያስ 27:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በኢየሩሳሌም ወደሚኖረው ወደ ይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ በመጡት መልእክተኞች በኩል ወደ ኤዶም፥ ሞአብ፥ ዐሞን፥ እንዲሁም ወደ ጢሮስና ሲዶና ነገሥታት መልእክት ላከ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሴዴቅያስ፣ ወደ ኢየሩሳሌም በመጡት ሰዎች በኩል ለኤዶም፣ ለሞዓብ፣ ለአሞን፣ ለጢሮስና ለሲዶና ነገሥታት መልእክት ላክ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ይሁዳ ንጉሥም ወደ ሴዴቅያስ ወደ ኢየሩሳሌም በመጡት መልእክተኞች እጅ ወደ ኤዶምያስ ንጉሥ፥ ወደ ሞዓብም ንጉሥ፥ ወደ አሞንም ልጆች ንጉሥ፥ ወደ ጢሮስም ንጉሥ፥ ወደ ሲዶናም ንጉሥ ትልካቸዋለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ይሁዳ ንጉሥም ወደ ሴዴቅያስ፥ ወደ ኢየሩሳሌም በመጡት መልእክተኞች እጅ ወደ ኤዶምያስ ንጉሥ፥ ወደ ሞዓብም ንጉሥ፥ ወደ አሞን ልጆች ንጉሥ፥ ወደ ጢሮስም ንጉሥ፥ ወደ ሲዶናም ንጉሥ ላክ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ይሁዳ ንጉሥም ወደ ሴዴቅያስ ወደ ኢየሩሳሌም በመጡት መልእክተኞች እጅ ወደ ኤዶምያስ ንጉሥ ወደ ሞዓብም ንጉሥ ወደ አሞንም ልጆች ንጉሥ ወደ ጢሮስም ንጉሥ ወደ ሲዶናም ንጉሥ ላካቸው። |
ሴዴቅያስ፥ ታማኝ እንዲሆንለት በእግዚአብሔር ስም ባስማለው በንጉሥ ናቡከደነፆር ላይ ዐመፀ፤ ተጸጽቶ ንስሓ በመግባት ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ በእልኸኛነት እምቢ አለ።
የሲዶና ከተማ ሆይ! አንቺ በባሕር አጠገብ የተገነባሽ ጠንካራ ምሽግ ነሽ፤ ነገር ግን አንቺ ባል አግብታ ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወልዳ እንዳላሳደገች ሴት የተዋረድሽ ትሆኚአለሽ።
ለይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስም ይህንኑ ቃል እንዲህ ብዬ ነገርኩት፦ “ለባቢሎን ንጉሥ ብትገብር፥ እርሱንና ሕዝቡንም ብታገለግል በሕይወት መኖር ትችላለህ፤
በዚሁ ዘመን፥ ማለትም ሴዴቅያስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት፥ በአምስተኛው ወር የገባዖን ሰው የሆነው የዐዙር ልጅ ሐናንያ በቤተ መቅደስ ተናገረኝ፤ በካህናቱና በሕዝቡ ሁሉ ፊት እንዲህ አለኝ፦
“የሰው ልጅ ሆይ! የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በጢሮስ ላይ አደጋ ለመጣል ተነሥቶአል፤ ራሳቸው እስኪመለጥና ትከሻቸው እስኪቈስል ወታደሮቹን ከባድ ሸክም እንዲሸከሙ አድርጎአቸዋል፤ ይሁን እንጂ ንጉሡም ሆነ ሠራዊቱ በዚህ ሁሉ ድካማቸው ምንም ያተረፉት ነገር የለም።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “የጢሮስ ሕዝብ ደጋግመው ስለ ሠሩት ኃጢአት ያለ ጥርጥር እቀጣቸዋለሁ፤ የገቡበትን የወንድምነት ቃል ኪዳን አፍርሰው የማረኳቸውን ሕዝቦች ለኤዶም አሳልፈው ሰጥተዋል፤