በኢዮስያስ ዘመነ መንግሥት ነኮ የተባለው የግብጽ ንጉሥ የአሦርን ንጉሠ ነገሥት ለመርዳት ሠራዊቱን እየመራ ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ ተጓዘ፤ ንጉሥ ኢዮስያስም መጊዶ ላይ የግብጽን ሠራዊት ለማገድ ጦርነት ገጥሞ በዚያ ውጊያ ላይ ተገደለ፤
ኤርምያስ 22:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም ተማርኮ በተወሰደበት አገር ስለሚሞት ዳግመኛ ተመልሶ ይህችን ምድር አያይም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተማርኮ በሄደበት አገር ይሞታል እንጂ ይህችን ምድር ዳግመኛ አያይም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በተማረከባት አገር በዚያ ይሞታል እንጂ፤ ይህችንም አገር ከእንግዲህ ወዲህ አያይም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በተማረከበት ሀገር ይሞታል፤ እንግዲህም ወዲህ ሀገሩን አያይም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህም ወደዚህ አይመለስም፥ በተማረከባት አገር ይሞታል እንጂ፥ ይህችንም አገር ከእንግዲህ ወዲህ አያይም። |
በኢዮስያስ ዘመነ መንግሥት ነኮ የተባለው የግብጽ ንጉሥ የአሦርን ንጉሠ ነገሥት ለመርዳት ሠራዊቱን እየመራ ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ ተጓዘ፤ ንጉሥ ኢዮስያስም መጊዶ ላይ የግብጽን ሠራዊት ለማገድ ጦርነት ገጥሞ በዚያ ውጊያ ላይ ተገደለ፤
ንጉሥ ኒካዑ የኢዮስያስ ልጅ ኤልያቄም በአባቱ በኢዮስያስ እግር ተተክቶ በይሁዳ እንዲነግሥ አደረገ፤ ስሙንም በመለወጥ ኢዮአቄም ብሎ ጠራው፤ ኢዮአሐዝም በንጉሥ ነኮ ተማርኮ ወደ ግብጽ ተወሰደ፤ በዚያም ሞተ።
ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ኢዮአቄም የሚለው ይህ ነው፥ “እርሱ በሚሞትበት ጊዜ ‘ዋይ! ወዮ! ወንድሜ ሆይ!’ እያሉ በማልቀስ አያዝኑለትም፤ እንዲሁም ‘ጌታዬ ሆይ! ንጉሤ ሆይ! ወዮ!’ እያለ የሚያለቅስለት አይኖርም።
“የሠራዊት ጌታ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ወደ ግብጽ እንሄዳለን ብላችሁ ብትወስኑ ከዚህ በፊት በኢየሩሳሌም ሕዝብ ላይ የወረደው ቊጣዬና መዓቴ በእናንተም ላይ ይወርዳል፤ ለሕዝብ ሁሉ አስፈሪ መቀጣጫ ትሆናላችሁ፤ የሚያዩአችሁም ሕዝብ ሁሉ መዘባበቻ ያደርጓችኋል፤ ስማችሁም ለመሳለቂያ ይሆናል፤ ይህችንም ስፍራ ዳግመኛ አታዩአትም።’ ”