ከተሰባበረ በኋላ ለእሳት መጫሪያ ወይም ለውሃ መጥለቂያ የሚሆን ከፍ ያለ ገል እንኳ ከመካከሉ እንደማይገኝበት ተንኰታኲቶ እንደሚወድቅ የሸክላ ዕቃ ትሆናላችሁ።”
ኤርምያስ 19:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አብረውኝ በሄዱት ሰዎች ፊት ያን ገንቦ እንድሰብረው አዘዘኝ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ገንቦውንም ከአንተ ጋራ በሄዱ ሰዎች ፊት ትሰብራለህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ገምቦውንም ከአንተ ጋር በሚሄዱ ሰዎች ፊት ትሰብራለህ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ገምቦውንም ከአንተ ጋር በሚሄዱ ሰዎች ፊት ትሰብራለህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ገምቦውንም ከአንተ ጋር በሚሄዱ ሰዎች ፊት ትሰብራለህ፥ |
ከተሰባበረ በኋላ ለእሳት መጫሪያ ወይም ለውሃ መጥለቂያ የሚሆን ከፍ ያለ ገል እንኳ ከመካከሉ እንደማይገኝበት ተንኰታኲቶ እንደሚወድቅ የሸክላ ዕቃ ትሆናላችሁ።”
እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “ሄደህ ከሸክላ ሠሪው ገንቦ ግዛ፤ ከሕዝቡና ከካህናቱ መካከል ታላላቆቹን መርጠህ ከአንተ ጋር አብረው እንዲሄዱ አድርግ።
አንድ ሰው የወይን ጠጅን ከአንድ ዕቃ ወደ ሌላ ዕቃ ገልብጦ ባዶውን ዕቃ እንደሚሰብር፥ እኔም ሞአብን የሚያወድምና ሕዝብዋን የሚያፈልስ ሰው የምልክበት ጊዜ በእርግጥ ተቃርቦአል።
በዚያም ኢየሱስ በማእድ ተቀምጦ ሳለ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ ሽቶ የሞላበት የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ ወደ እርሱ ቀረበች፤ ሽቶውንም በራሱ ላይ አፈሰሰችው።