አሁንም እግዚአብሔር ሆይ፤ የደረሰብንን ነገር ሁሉ ተመልከት፥ ሕያው አምላክን አንተን በመስደብ ሰናክሬም የተናገረውን የዛቻ ቃል ሁሉ አድምጥ፤
ኤርምያስ 18:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እንዲህ በማለት ጸለይኩ “እግዚአብሔር ሆይ! ልመናዬን ስማ፤ ጠላቶቼም በእኔ ላይ የሚናገሩትን ክፉ ነገር አድምጥ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ስማኝ፤ ባላንጣዎቼ የሚሉትን አድምጥ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ! አድምጠኝ፥ ጠላቶቼ ምን እደሚሉ ስማ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አቤቱ! አድምጠኝ፤ የክርክሬንም ቃል ስማ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤቱ፥ አድምጠኝ፥ የክርክሬንም ቃል ስማ። |
አሁንም እግዚአብሔር ሆይ፤ የደረሰብንን ነገር ሁሉ ተመልከት፥ ሕያው አምላክን አንተን በመስደብ ሰናክሬም የተናገረውን የዛቻ ቃል ሁሉ አድምጥ፤
ከሕዝቡ መካከል አንዳንድ ሰዎች፦ “ኑ በኤርምያስ ላይ ዕቅድ እናውጣ! የእግዚአብሔርን ሕግ የሚያስተምሩ ካህናት፥ ምክር የሚሰጡ ጥበበኞች፥ የእግዚአብሔርን መልእክት የሚናገሩ ነቢያት ሁልጊዜ እናገኛለን፤ ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲያ ኤርምያስን ከማድመጥ ይልቅ በንግግሩ አጥምደን በወንጀል እንክሰሰው ተባባሉ።”
ታዲያ የደግ ሥራ ዋጋው ክፉ ነገር ማድረግ ነውን? አንተ በእነርሱ ላይ እንዳትቈጣ እኔ በፊትህ ቆሜ ስለ እነርሱ እንደማለድኩህ አስብ፤ እነርሱ ግን እነሆ እኔ የምወድቅበትን ጒድጓድ ቈፈሩ።
የሠራዊት አምላክ ሆይ! ጻድቅን ፈትነህ ታረጋግጣለህ፤ የልብንም ጥልቅ ሐሳብ ትመረምራለህ፤ አቤቱታዬን ለአንተ አቅርቤአለሁ፤ ስለዚህ ጠላቶቼን ስትበቀል እንዳይ አድርገኝ።