ኤርምያስ 18:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእግዚአብሔር ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፦ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከጌታ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል፥ እንዲህም አለው፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል፥ እንዲህም አለው፦ ተነሥተህ ወደ ሸክላ ሠሪው ቤት ውረድ፥ በዚያም ቃሌን አሰማሃለሁ። |
እናንተ ሁሉን ነገር ትገለባብጣላችሁ። ሸክላ ሠሪው ከሸክላው አይበልጥምን? አንድ የተሠራ ሥራ ሠሪውን “አንተ አልሠራኸኝም” ይለዋልን? ወይስ ደግሞ የሸክላ ዕቃ ሸክላ ሠሪውን “ሥራህን አታውቅም” ይለዋልን?
ነገር ግን ለእኔ መታዘዝና ሰንበትንም የተቀደሰ ቀን አድርገው ማክበር ይገባቸዋል፤ በዚህ ዕለት በኢየሩሳሌም የቅጽር በሮች ምንም ዐይነት ሸክም ይዘው መግባት የለባቸውም፤ ትእዛዜን ባለመቀበል ይህን ቢያደርጉ ግን የኢየሩሳሌም ቅጽር በሮች በእሳት እንዲጋዩ አደርጋለሁ፤ የኢየሩሳሌም ቤተ መንግሥቶችም በእሳት ይነዳሉ፤ እሳቱንም ሊያጠፋ የሚችል የለም።’ ”