ኤርምያስ 15:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የይሁዳ ሕዝብ ሆይ! ከነሐስ ጋር የተቀላቀለን ብረት ለመስበር እንደማትችሉ ሁሉ በሰሜን በኩል ከጠላት የተቃጣውን አደጋ ልታሸንፉ አትችሉም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሰው ብረትን፣ ከሰሜን የመጣን ብረት፣ ንሓስንስ መስበር ይችላልን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በውኑ ብረትን፥ የሰሜንን ብረት፥ ናስንም የሚሰብር አለን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በውኑ ብረትን፥ የሰሜንን ብረት፥ ናስንም የሚሰብር አለን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውኑ ብረትን፥ የሰሜንን ብረት፥ ናስንም የሚሰብር አለን? |
ከሠሪው ጋር ለሚከራከር ወዮለት! እርሱ እኮ ከሸክላ ዕቃዎች እንደ አንዱ ነው፤ አንድ የሸክላ ሥራ ሸክላ ሠሪውን “ምንድን ነው የምታደርገው? እጀታውስ የት አለ?” ብሎ ሊጠይቅ ይችላልን?
በእነዚህ ሕዝቦች ሁሉ ጫንቃ ላይ የብረት ቀንበር እጭናለሁ፤ እነርሱም ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር ይገዙለታል፤ ሌላው ቀርቶ የምድረ በዳ እንስሶች ሁሉ እንዲገዙለት አደርጋለሁ፤’ እኔ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ይህን ተናግሬአለሁ።”