Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 15:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “በመላ ሀገሪቱ በፈጸማችሁት ኃጢአት ምክንያት ሀብታችሁንና ንብረታችሁን ያለ አንዳች ማካካሻ ለጠላት አሳልፌ እሰጣለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 በመላ አገርህ፣ ስላለው ኀጢአትህ ሁሉ፣ ሀብትና ንብረትህን፣ ያለ ዋጋ አሳልፌ ለምርኮ እሰጣለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 “በመላ ግዛቶችህ ውስጥ ስላለ ኃጢአትህ ሁሉ ባለጠግነትህንና መዝገብህን ለብዝበዛ በከንቱ አሳልፌ እሰጣለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 በዳ​ር​ቻህ ሁሉ ስላለ ኀጢ​አ​ትህ ሁሉ ፋንታ ባለ​ጠ​ግ​ነ​ት​ህ​ንና መዝ​ገ​ብ​ህን ለመ​በ​ዝ​በዝ በከ​ንቱ እሰ​ጣ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 በዳርቻህ ሁሉ ስላለ ኃጢአትህ ሁሉ ባለጠግነትህንና መዝገብህን ለመበዝበዝ በከንቱ እሰጣለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 15:13
8 Referencias Cruzadas  

ሕዝብህን በአነስተኛ ዋጋ ሸጥከው፤ እርሱንም በመሸጥ ምንም አላተረፍክም።


እግዚአብሔር ሕዝቡን እንዲህ ይላል፦ “ለባርነት ያለ ዋጋ ተሸጣችሁ ነበር፤ የምትዋጁትም ዋጋ ሳይከፈል ነው።


“ሕዝቤ ያለ ዋጋ ሲወሰድ እያየሁ አሁን እኔ የማደርገው ምን አለ? ገዢዎቻቸውም ይሳለቁባቸዋል፤ ያለማቋረጥም ስሜን ይሰድባሉ።


በምድራችሁ ላይ የሚገኙት ባሎቻቸው የሞቱባቸው ሴቶች ብዛታቸው ከባሕር አሸዋ የሚበልጥ ሆኖአል፤ በእኩለ ቀን በወጣቶች እናቶች ላይ ሞትን አመጣለሁ በእነርሱም ላይ ሽብርንና ጭንቀትን በቅጽበት አመጣለሁ።


በመላ አገራችሁ በፈጸማችሁት ከፍተኛ ኃጢአት ምክንያት ያላችሁን ሀብትና ንብረት እንዲሁም መሠዊያዎቻችሁን ሁሉ በምርኮ ጠላቶቻችሁ እንዲወስዱ አደርጋለሁ።


እንዲሁም ጠላቶቻቸው የዚህችን ከተማ ሀብት ሁሉ እንዲዘርፉት፥ ያካበተችውንም ሀብትና ንብረት አጋብሰው የይሁዳን ነገሥታት የሀብት መዛግብት እንኳ ሳይቀር ጠራርገው ወደ ባቢሎን እንዲወስዱት አደርጋለሁ፤


ሳባና ዴዳን፥ እንዲሁም የተርሴስ ነጋዴዎችና ወጣት ጦረኞች እንዲህ ይሉሃል፦ ‘ምርኮን ለመውሰድ መጣህን? ብርንና ወርቅን፥ እንስሶችና ቈሳቊስን፥ ማለት ብዙ ምርኮን እንዲያጓጒዙልህ ብዛት ያላቸውን ሰዎችህን ሰበሰብክን?’ ”


ሀብታቸው ይዘረፋል፤ ቤቶቻቸውም ይፈርሳሉ፤ በዚያን ጊዜ ቤት ይሠራሉ፤ ነገር ግን አይኖሩበትም፤ ወይንም ይተክላሉ፤ ነገር ግን የወይኑን ጠጅ አይጠጡም።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos