La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 14:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዝናብ ከመጥፋቱ የተነሣ፥ ምድር ትደርቃለች፤ ገበሬዎችም ተስፋ በመቊረጥ፥ በሐዘን ራሳቸውን ይሸፍናሉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በምድሪቱ ዝናብ ስለሌለ፣ መሬቱ ተሰነጣጥቋል፤ ገበሬዎችም ዐፍረው፣ ራሳቸውን ተከናንበዋል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በምድር ላይ አልዘነበምና መሬቱ ስንጥቅጥቅ ስለሆነ አራሾች አፈሩ ራሳቸውንም ተከናነቡ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በም​ድር ላይ አል​ዘ​ነ​በ​ምና መሬቱ ስን​ጥ​ቅ​ጥቅ ስለ ሆነ አራ​ሾች ዐፈሩ፤ ራሳ​ቸ​ው​ንም ተከ​ና​ነቡ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በምድር ላይ አልዘነበምና መሬቱ ስንጥቅጥቅ ስለሆነ አራሾች አፈሩ ራሳቸውንም ተከናነቡ።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 14:4
10 Referencias Cruzadas  

እጅሽን በራስሽ ላይ አድርገሽ በዕፍረት ከዚያ ቦታ ትሄጂአለሽ፤ እኔ እግዚአብሔር አንቺ የምትታመኝባቸውን ሁሉ ስላስወገድኩ ከእነርሱ የምታገኚው ምንም ነገር አይኖርም።”


የበልጉም ሆነ የክረምት ዝናብ ሊቀር የቻለው በዚህ ምክንያት ነው፤ አንቺ ዐይነ ዐፋርነትን አስወግደሽ እንደ አመንዝራ ሴት ኀፍረተቢስ ሆነሻል።


ስንዴውና ገብሱ፥ ሌላውም መከር ሁሉ ስለ ጠፋ፥ እናንተ ገበሬዎች እዘኑ፤ እናንተም የወይን ተክል ባለቤቶች አልቅሱ።


የተዘራው እህል ሁሉ በዐፈር ውስጥ በስብሶ ቀርቶአል፤ እህል በመታጣቱ የእህል ማከማቻዎች ሁሉ ባዶ ሆነዋል፤ ጐተራዎችም ፈራርሰዋል።


“ይህም ሁሉ ከደረሰባችሁ በኋላ እንኳ የማትታዘዙኝ ከሆናችሁ፥ በእናንተ ላይ የማመጣውን ቅጣት ሰባት ጊዜ እጥፍ እንዲበዛ አደርገዋለሁ።


ሰዎች ውሃ መጠጣት ፈልገው ከከተማ ወደ ከተማ ሄዱ፤ ነገር ግን በቂ ውሃ ባለማግኘታቸው ጠጥተው ሊረኩ አልቻሉም፤ እናንተም ወደ እኔ አልተመለሳችሁም።


ምድሪቱም ሁሉ በዲንና በጨው ትሸፈናለች፤ ምንም ነገር አይተከልባትም፤ ምንም ነገር አታበቅልም፤ እግዚአብሔር በኀይለኛ ቊጣው እንደ ደመሰሳቸው እንደ ሰዶምና ገሞራ፥ እንደ አዳማና እንደ ጺባዮ ትሆናለች።