እኛ ሁላችን በኃጢአት ረክሰናል፤ ጽድቃችንም እንደ አደፍ ጨርቅ ሆኖአል፤ ከኃጢአታችን ብዛት የተነሣ ደርቀው በነፋስ እንደሚረግፉ ቅጠሎች ሆነናል።
ኤርምያስ 13:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔም ሄጄ መታጠቂያውን የደበቅሁበትን ስፍራ አገኘሁ፤ መታጠቂያውንም ባየሁት ጊዜ ተበላሽቶና ከጥቅም ውጪ ሆኖ አገኘሁት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔም ወደ ኤፍራጥስ ሄጄ፣ መታጠቂያውን ከሸሸግሁበት ቦታ ቈፍሬ አወጣሁ፤ መታጠቂያውም ተበላሽቶ፣ ከጥቅም ውጭም ሆኖ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም ወደ ኤፍራጥስ ሄድሁ ቆፈርሁም፥ ከዚያ ከሸሸግሁበትም ስፍራ መታጠቂያውን ወሰድሁ። እነሆም፥ መታጠቂያው ተበላሽቶ ነበር፥ ለምንም አይረባም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ ሄድሁ፤ ቈፈርሁም፤ ከቀበርሁበትም ስፍራ መታጠቂያዪቱን ወሰድሁ። እነሆም መታጠቂያዪቱ ተበላሽታ ነበር፤ ለምንም አልረባችም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም ወደ ኤፍራጥስ ሄድሁ ቆፈርሁም፥ ከሸሸግሁበትም ስፍራ መታጠቂያይቱን ወሰድሁ። እነሆም፥ መታጠቂያይቱ ተበላሽታ ነበር፥ ለምንም አልረባችም። |
እኛ ሁላችን በኃጢአት ረክሰናል፤ ጽድቃችንም እንደ አደፍ ጨርቅ ሆኖአል፤ ከኃጢአታችን ብዛት የተነሣ ደርቀው በነፋስ እንደሚረግፉ ቅጠሎች ሆነናል።
እነዚህ በክፋት የተሞሉ ሕዝብ ለእኔ መታዘዝን እምቢ ብለዋል፤ ከምንጊዜውም ይልቅ እልኸኞች ሆነዋል፤ ባዕዳን አማልክትን በማምለክ ያገለግላሉ፤ ከዚህም የተነሣ እነርሱ ዋጋቢስ ሆኖ እንደ ቀረው እንደዚያ መታጠቂያ ይሆናሉ።