ኤርምያስ 13:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እግዚአብሔር ባዘዘኝ መሠረት ሄጄ በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ መታጠቂያውን ደበቅሁት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እግዚአብሔር በነገረኝ መሠረት ወደ ኤፍራጥስ ሄጄ ሸሸግሁት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም እንዳዘዘኝ ሄድሁ በኤፍራጥስም አጠገብ ሸሸግሁት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም እንዳዘዘኝ ሄድሁ፤ በኤፍራጥስም ወንዝ አጠገብ ሸሸግኋት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም እንዳዘዘኝ ሄድሁ በኤፍራጥስም አጠገብ ሸሸግኋት። |
እኔም በታዘዝኩት መሠረት ትንቢት ተናገርኩ፤ መናገርም እንደ ጀመርኩ የመንኰሻኰሽ ድምፅ ሰማሁ፤ አጥንቶቹም እርስ በርሳቸው እየተገጣጠሙ መያያዝ ጀመሩ።
አብርሃም ወጥቶ ርስት አድርጎ ወደሚቀበለው ስፍራ እንዲሄድ በተጠራ ጊዜ ምንም እንኳ ወዴት እንደሚሄድ ባያውቅም ለመሄድ የታዘዘው በእምነት ነው።