ኤርምያስ 11:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ከሆነ አሁን ያሉባትን በማርና በወተት የበለጸገችውን ለምለም ምድር የቀድሞ አባቶቻቸው እንዲወርሱ ባደረግሁ ጊዜ የሰጠኋቸውን የተስፋ ቃል እፈጽማለሁ።” እኔም “እሺ ጌታ ሆይ!” አልኩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዛሬም እንደ ሆነው ሁሉ ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር ለአባቶቻችሁ ለመስጠት የገባሁትን መሐላ እፈጽማለሁ።’ ” እኔም፣ “እግዚአብሔር ሆይ፤ አሜን” ብዬ መለስሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህ ዛሬ እንደሆነ ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር ለአባቶቻችሁ እንድሰጣቸው የማልሁትን መሐላ እንዳጸና ነው።” እኔም፦ “አቤቱ! አሜን” ብዬ መለስሁለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህም ዛሬ እንደ ሆነ ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር እሰጣቸው ዘንድ ለአባቶቻችሁ የማልሁትን መሐላ አጸና ዘንድ ነው። እኔም፥ “አቤቱ! ጌታ ሆይ! ይሁን” ብዬ መለስሁለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህም ዛሬ እንደ ሆነ ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር እሰጣቸው ዘንድ ለአባቶቻችሁ የማልሁትን መሐላ አጸና ዘንድ ነው። እኔም፦ አቤቱ፥ አሜን ብዬ መለስሁለት። |
የከነዓናውያንን፥ የሒታውያንን፥ የአሞራውያንን፥ የሒዋውያንንና የኢያቡሳውያንን ምድር እንደሚያወርሳችሁ እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶቻችሁ በመሐላ ቃል ኪዳን ገብቶአል፤ በማርና በወተት ወደ በለጸገችው ወደዚያች ለም ምድር በሚያገባችሁ ጊዜ በዓመቱ መጀመሪያ ወር ላይ ይህን በዓል ታከብሩታላችሁ።
“አሜን! እግዚአብሔር እንዳልከው ያድርግ! የቤተ መቅደሱን ዕቃዎች በማምጣትና የተማረኩትን ምርኮኞች በመመለስ እግዚአብሔር አንተ የተናገርከውን ትንቢት ይፈጽም።
ነገር ግን ምድራቸውን ትወርሳላችሁ፤ በማርና በወተት የበለጸገችውን ምድር እንድትወርሱ እሰጣችኋለሁ፤ ከሌሎች ሕዝቦች እንድትለዩ ያደረግኋችሁ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።
እንዲህማ ካልሆነ አንተ በመንፈስ እግዚአብሔርን ስታመሰግን፥ አንተ የምትለውን የማያውቅ እንግዳ ሰው ለምስጋና ጸሎትህ “አሜን” ሊል እንዴት ይችላል?
የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! እነዚህን ሕግጋት አድምጡ! ታዘዙላቸውም! ይህን ብታደርጉ ለቀድሞ አባቶቻችሁ እግዚአብሔር በሰጠው ተስፋ መሠረት በማርና በወተት በበለጸገች በዚያች ለም ምድር ሁሉ ነገር በመልካም ሁኔታ ይከናወንላችኋል፤ ትበዛላችሁም።