ኤርምያስ 1:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ግን እንዲህ አለኝ፦ “ ‘ገና ልጅ ነኝ’ አትበል፤ የምትሄደው እኔ ወደምልክህ ቦታ ነው፤ የምትናገረውም እኔ የማዝህን ሁሉ ነው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ግን እንዲህ አለኝ፤ “ ‘ገና ሕፃን ልጅ ነኝ’ አትበል፤ ወደምልክህ ሁሉ ሄደህ፣ ያዘዝሁህን ሁሉ ትናገራለህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ግን እንዲህ አለኝ፦ “ ‘ብላቴና ነኝ’ አትበል፤ ወደ ምልክህ ሁሉ ትሄዳለህ፥ የማዝህንም ሁሉ ትናገራለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ግን እንዲህ አለኝ፥ “ወደምልክህ ሁሉ ዘንድ ትሄዳለህና፥ የማዝዝህንም ሁሉ ትናገራለህና፦ ሕፃን ነኝ አትበል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ግን እንዲህ አለኝ፦ ወደምሰድድህ ሁሉ ዘንድ ትሄዳለህና፥ የማዝዝህንም ሁሉ ትናገራለህና፦ ብላቴና ነኝ አትበል። |
እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! እነሆ እኔ በዕድሜ አነስተኛ ነኝ፤ የአመራር ልምድም የለኝም፤ አንተ ግን በአባቴ እግር ተተክቼ እንድነግሥ ፈቃድህ ሆኖአል፤
ዳግመኛ ስናገርህና አንደበትህን ስከፍትልህ እንዲህ ትላቸዋለህ፦ “ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘እነርሱ ዐመፀኞች ስለ ሆኑ ለመስማት የሚፈቅዱ ይስሙ፥ ለመስማት የማይፈቅዱ ይተዉት።’ ”
በዚያን ሌሊት እግዚአብሔር ወደ በለዓም መጣና “እነዚህ ሰዎች ወደ አንተ የመጡት ይዘውህ ሊሄዱ ከሆነ ተነሥተህ አብረሃቸው ሂድ፤ ነገር ግን እኔ የምነግርህን ብቻ አድርግ” አለው።
በለዓምም “ያም ሆነ ይህ አሁን መጥቼ የለምን? ታዲያ አሁንስ ቢሆን በራሴ ምን ኀይል አለኝ? እኔ ልናገር የምችለው እግዚአብሔር የሚነግረኝን ብቻ ነው” ሲል መለሰለት።