ኢሳይያስ 8:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያ በኋላ ወደ ምድር ሲመለከቱ ሊያዩ የሚችሉት ጭንቀት ጨለማና ጭፍግግ ያለ አስፈሪ ሁኔታን ነው፤ ወደ ድቅድቅ ጨለማም ይጣላሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ወደ ምድር ይመለከታሉ፣ የሚያዩትም ጭንቀት፣ ጨለማና የሚያስፈራም ጭጋግ ብቻ ነው፤ ወደ ድቅድቅ ጨለማም ይጣላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ወደ ምድር ይመለከታሉ፤ የሚያዩትም ጭንቀት፤ ጨለማና የሚያስፈራም ጭጋግ ብቻ ነው፤ ወደ ድቅድቅ ጨለማም ይጣላሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ታችም ወደ ምድር ትመለከታላችሁ፤ ድቅድቅ ጨለማንም ታያላችሁ፤ ታላቅ መከራንም ትቀበላላችሁ፤ ትጨነቃላችሁ፤ ትቸገራላችሁም፤ በፊታችሁም ጨለማ ይሆናል፤ አታዩምም፤ በመከራም ያለ ጊዜው እስኪደርስ አይድንም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ምድርም ይመለከታሉ፥ እነሆም፥ መከራና ጨለማ የሚያስጨንቅም ጭጋግ አለ፥ ወደ ድቅድቅም ጨለማ ይሰደዳሉ። |
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን “እጅህን ወደ ሰማይ ዘርጋው፤ በእጅ እስከሚዳሰስ ድረስ ጥቅጥቅ ያለ ጨለማ የግብጽን ምድር ይሸፍናል” አለው።
በደቡባዊ በረሓ ስለሚኖሩ እንስሶች የተነገረ የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፦ “መልእክተኞቹ የአንበሶች መኖሪያ፥ የመርዘኛ እባቦችና የበራሪ ዘንዶዎች መስለክለኪያ በሆነ አደገኛ አገር አቋርጠው ይሄዳሉ፤ በአህዮቻቸውና በግመሎቻቸው ውድ የሆኑ ስጦታዎችን ጭነው ምንም ርዳታ ልትሰጣቸው ወደማትችል አገር ይሄዳሉ።
በዚያን ቀን እንደ ባሕር ማዕበል እየተመሙ በእስራኤል ሕዝብ ላይ ይመጡባቸዋል፤ እነሆ ወደ ምድር ቢመለከቱ በጨለማና በመከራ እንደ ተከበቡ ያያሉ፤ ከደመናውም የተነሣ ብርሃኑ ይጨልማል።
እናንተ ሁላችሁም ነገር በሰው ላይ እንደ እሳት የምታነዱና እንደ ችቦ የምትለኲሱ ናችሁ፤ ባነደዳችሁት እሳት ነበልባል ውስጥና በለኰሳችሁት ችቦ ትጠፋላችሁ ይህንንም ቅጣት የምትቀበሉት ከእኔ ነው።
ሕዝቡ እንዲህ ይላሉ፦ “ፍትሕ ከእኛ ርቆአል፤ ጽድቅም ወደ እኛ አይደርስም፤ ብርሃን እንዲበራልን እንፈልጋለን፤ ነገር ግን ሁሉም ጨለማ ነው፤ ስለዚህ በድቅድቅ ጨለማ እንመላለሳለን።
እነዚያ የተሠቃዩት ግን ዳግመኛ ችግር አይደርስባቸውም። በቀድሞ ዘመን የዛብሎንና የንፍታሌም ምድር ተዋርዳ ትኖር ነበር፤ በኋለኛው ዘመን ግን ከሜዲቴራኒያን ባሕር ምሥራቅ ጀምሮ እስከ ዮርዳኖስ ማዶ ያለው በተለይም አሕዛብ ሰፍረውበት የነበረው የገሊላ ምድር ክብርን ይጐናጸፋል።
በአንድ በኩል ሆዳቸው እስኪሞላ ይበላሉ፤ ነገር ግን እንደ ተራቡ ናቸው፤ እንዲሁም በሌላ በኩል አግበስብሰው ይውጣሉ፤ ነገር ግን አይጠግቡም፤ የልጆቻቸውን ሥጋ እንኳ እስከ መብላት ይደርሳሉ።
ጨለማን አምጥቶ በተራራዎች ከመሰናከላችሁ በፊት ተስፋ ያደረጋችኹትን ብርሃን ወደ ድቅድቅ ጨለማና ወደ ጥልቅ ጭጋግ ከመለወጡ በፊት አምላካችሁን እግዚአብሔርን አክብሩ።
ስለዚህም መንገዳቸው የሚያዳልጥ መሬት ይሆናል፤ በጨለማም ሲራመዱ መንገዳቸውን ስተው ይወድቃሉ፤ በሚቀጡበትም ቀን ክፉ ነገርን አመጣባቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።
“ከነዚያ ከመከራ ቀኖች በኋላ ወዲያውኑ ፀሐይ ትጨልማለች፤ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፤ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፤ የሰማያት ኀይሎችም ይናወጣሉ።
የአሳፋሪ ድርጊታቸውን ዐረፋ የሚደፍቁ፥ እንደ ተቈጣ የባሕር ማዕበል ናቸው፤ ድቅድቅ ጨለማ ለዘለዓለም እንደሚጠብቃቸውና፥ እንደሚንከራተቱ ኮከቦች ናቸው።
አምስተኛው መልአክ ጽዋውን በአውሬው ዙፋን ላይ አፈሰሰ፤ የአውሬውም መንግሥት ጨለማ ሆነ፤ ሰዎች ከሥቃያቸው የተነሣ ምላሳቸውን ያኝኩ ነበር፤