ኢሳይያስ 66:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የምፈጥራቸው አዲስ ሰማያትና አዲስ ምድር በእኔ ጸንተው እንደሚኖሩ እንዲሁም ዘራችሁና ስማችሁ በእኔ ጸንተው ይኖራሉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እኔ የምሠራቸው አዲስ ሰማያትና አዲስ ምድር በፊቴ ጸንተው እንደሚኖሩ፣ የእናንተና የዘራችሁ ስም እንደዚሁ ጸንቶ ይኖራል” ይላል እግዚአብሔር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ የምሠራቸው አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ከፊቴ ጸንተው እንደሚኖሩ፥ እንዲሁ ዘራችሁና ስማችሁ ጸንተው ይኖራሉ፥ ይላል ጌታ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እኔ የምሠራቸው አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር በፊቴ ጸንተው እንደሚኖሩ፥ እንዲሁ ዘራችሁና ስማችሁ ጸንተው ይኖራሉ፥ ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ የምሠራቸው አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ከፊቴ ጸንተው እንደሚኖሩ፥ እንዲሁ ዘራችሁና ስማችሁ ጸንተው ይኖራሉ፥ ይላል እግዚአብሔር። |
ቃሌን በአንደበትሽ አሳድራለሁ፤ አንቺንም በእጄ ጥላ ሥር እጋርድሻለሁ፤ ሰማያትን የዘረጋሁ፥ ምድርንም የመሠረትኩ እኔ ነኝ፤ ጽዮንንም ‘አንቺ ሕዝቤ ነሽ’ እላታለሁ።”
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ይሁን እንጂ በሕማም አደቀው ዘንድ የእኔ ፈቃድ ነበር፤ ሕይወቱን የበደል መሥዋዕት አድርጎ በሚያቀርብበት ጊዜ ዘመኑ ተራዝሞ ብዙ ትውልድ ያያል፤ በእርሱም አማካይነት የእኔ ፈቃድ ይፈጸማል።
ለእነርሱ በቤተ መቅደሴና በግቢዬ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች የተሻለ መታሰቢያ እንዲኖራቸው አደርጋለሁ፤ የማይረሳ ዘላቂ መታወቂያም እሰጣቸዋለሁ።”
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ከእነርሱ ጋር የሚኖረኝ ቃል ኪዳን ይህ ነው፦ ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘለዓለም በእናንተ ላይ ያለው መንፈሴና በአንደበታችሁ ያኖርኩትን ቃሌን ለልጆቻችሁና ለልጅ ልጆቻችሁ አስተምሩ ይላል እግዚአብሔር።”
እኔ እግዚአብሔር ፍትሕን እወዳለሁ፤ ቅሚያንና ክፉ ድርጊትን እጠላለሁ፤ እኔ ተገቢ ዋጋቸውን እሰጣቸዋለሁ፤ ከእነርሱም ጋር ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን እገባለሁ።
ልጆቻቸው በወገኖች ዘንድ፥ የልጅ ልጆቻቸውም በሕዝቦች ዘንድ የታወቁ ይሆናሉ። የሚያዩአቸው ሁሉ በእኔ በእግዚአብሔር የተባረኩ ዘሮች መሆናቸውን ያውቃሉ።
እነርሱ የሠሩትን ቤት ሌሎች አይገቡበትም፤ የተከሉትንም ማንኛውንም ነገር ባዕዳን አይበሉትም፤ ሕዝቤ እንደ ዛፍ ለረጅም ዘመናት ይኖራሉ፤ የመረጥኳቸውም ሰዎች የደከሙበትን ነገር ለረጅም ጊዜ ይደሰቱበታል።
ሥራቸው ከንቱ አይሆንም፤ የወለዱአቸው ልጆችና የልጅ ልጆቻቸው በእግዚአብሔር የተባረኩ ስለሚሆኑ ልጆቹን የሚወልዱት ጥፋት እንዲደርስባቸው አይደለም።
“ለአገልጋዬ ለዳዊት ዙፋን የሚወርስ ልጅ እንደምሰጠው የገባሁት ቃል ኪዳንና ለአገልጋዮቼ ለሌዋውያን ስለሚሰጡኝ አገልግሎት ያቆምኩላቸው ቃል ኪዳን ሊፈርሱ የሚችሉት ቀንና ሌሊት በተወሰነላቸው ጊዜ እንዲመጡ ያቆምኩላቸውን ሥርዓት ከእናንተ መካከል ለማፍረስ የሚችል ሰው የተገኘ ከሆነው ነው።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በዚያን ጊዜ ሰብስቤ ወደ ሀገራችሁ እመልሳችኋለሁ፤ ንብረታችሁን ሁሉ ዐይናችሁ እያየ በምመልስላችሁ ጊዜ በምድር ሕዝቦች ሁሉ ፊት ዝነኞችና የተመሰገናችሁ ትሆናላችሁ።”
ከዚህ በኋላ አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር አየሁ፤ የመጀመሪያው ሰማይና የመጀመሪያይቱ ምድር አልፈው ነበር፤ ባሕርም ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም።