ኢሳይያስ 43:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ የእስራኤል ቅዱስ እግዚአብሔር አምላካችሁና አዳኛችሁ ነኝ፤ እናንተን ለመታደግ ግብጽን፥ ኢትዮጵያውያንንና ሳባን እሰጣለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ እግዚአብሔር አምላክህ፣ የእስራኤልም ቅዱስ መድኀኒትህ ነኝና፤ ግብጽን ለአንተ ቤዛ እንድትሆን፣ ኢትዮጵያንና ሳባን በአንተ ፈንታ እሰጣለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ የእስራኤል ቅዱስ አምላክህ ጌታ መድኃኒትህ ነኝ፤ ግብጽን ለአንተ ቤዛ አድርጌ፥ ኢትዮጵያንና ሳባንም ለአንተ ፋንታ እሰጣለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ የእስራኤል ቅዱስ አምላክህ እግዚአብሔር መድኀኒትህ ነኝ፤ ግብፅንና ኢትዮጵያን ለአንተ ቤዛ አድርጌ፥ ሴዎንንም ለአንተ ፋንታ ሰጥቻለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ የእስራኤል ቅዱስ አምላክህ እግዚአብሔር መድኃኒትህ ነኝ፥ ግብጽን ለአንተ ቤዛ አድርጌ፥ ኢትዮጵያንና ሳባንም ለአንተ ፋንታ ሰጥቻለሁ። |
መኳንንቱም ንጉሡን እንዲህ አሉት፤ “ይህ ሰው ለእኛ ወጥመድ ሆኖ የሚያስቸግረን እስከ መቼ ነው? አምላካቸውን እግዚአብሔርን ያገለግሉ ዘንድ ከእስራኤላውያን ወገን ወንዶቹ ይሂዱ፤ አገሪቱ በመጥፋት ላይ መሆንዋ አይታወቅህምን?”
በደጋግ ሰዎች ላይ ሊደርስ የነበረው ችግር በክፉ ሰዎች ላይ ይደርሳል፤ በቀጥተኛ ሰዎች ላይ ሊደርስ የነበረው ችግር በእምነተ ቢሶች ላይ ይመጣል።
እነርሱም የሠራዊት አምላክ በግብጽ ምድር ለመኖሩ ምልክትና ምስክር ይሆናሉ፤ በዚያ የሚኖሩ ሕዝቦች ችግር ሲደርስባቸው እግዚአብሔር እንዲረዳቸው በሚጠይቁበት ጊዜ የሚታደጋቸውን አዳኝ ይልክላቸዋል፤ እርሱም ከጠላቶቻቸው ያድናቸዋል።
እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “አገልጋዬ ኢሳይያስ ዕራቊቱን በባዶ እግሩ ሦስት ዓመት ሙሉ ሲመላለስ ነበር፤ በግብጽና በኢትዮጵያ ላይ የሚደርስባቸውም ምልክት ይኸው ነው።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የግብጽ ሀብትና የኢትዮጵያ ሸቀጥ ለእናንተ ተላልፎ ይሰጣል፤ ቁመታቸው ረጃጅም የሆነ የሳባ ሰዎችም በሰንሰለት ታስረው በመምጣት ይከተሉአችኋል፤ እጅ ነሥተውም፦ ‘እግዚአብሔር የሚገኘው በእናንተ ዘንድ ብቻ ነው፤ በሌላ አይደለም፤ ከእርሱም በቀር ሌላ አምላክ የለም’ ይላሉ።”
ጉዳይህን አቅርበህ ገለጻ አድርግ፤ ከብዙ ጊዜ በፊት ይህን የተናገሩ ተሰብስበው ይመካከሩ፤ በጥንት ጊዜ የተናገረው ማነው? እኔ እግዚአብሔር አልነበርኩምን? ከእኔ በቀር ጻድቅና አዳኝ አምላክ የለም።
ጨቋኞችሽ የገዛ ሥጋቸውን እንዲበሉ አደርጋለሁ፤ በወይን ጠጅ እንደሚሰክሩ የገዛ ደማቸውን ጠጥተው እንዲሰክሩ አደርጋለሁ። ከዚህም የተነሣ እኔ እግዚአብሔር አዳኝሽና ታዳጊሽ የእስራኤል ኀያል አምላክ መሆኔን የዓለም ሕዝብ ሁሉ ያውቃል።”
ልጆች የእናታቸውን ጡት እንደሚጠቡ የአንቺም ልጆች የሕዝቦችንና የነገሥታትን ሀብት በመውሰድ ይጠቀሙበታል፤ አንቺም እኔ እግዚአብሔር አዳኝሽና ታዳጊሽ ኀያሉ የያዕቆብ አምላክ መሆኔን ታውቂአለሽ።
የእስራኤል ተስፋ አንተ ብቻ ነህ፤ ከመቅሠፍት የምታድነንም አንተ ነህ፤ ታዲያ በምድራችን እንደ እንግዳ፥ ለአንድ ቀን እንደሚያድር መንገደኛስ የሆንከው ለምንድን ነው?
ቅዱስ ስሜ በሕዝቤ በእስራኤል ዘንድ እንዲታወቅ አደርጋለሁ፤ ከእንግዲህም ወዲህ ስሜ እንዲሰደብ አልፈቅድም፤ ከዚያም በኋላ ሕዝቦች ሁሉ እኔ እግዚአብሔር የእስራኤል ቅዱስ መሆኔን ያውቃሉ።”
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ አምላካችሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የላችሁም፤ አዳኛችሁም እኔ ብቻ ነኝ።
እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ፤ እኔ ቅዱስ ስለ ሆንኩ እናንተም ራሳችሁን የተቀደሰ አድርጉ፤ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱትን ነፍሳት በመብላት ራሳችሁን አታርክሱ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! በእኔ ዘንድ ኢትዮጵያውያን ከእናንተ አያንሱም፤ እናንተን ከግብጽ እንዳወጣሁ እንደዚሁም ፍልስጥኤማውያንን ከቀርጤስ፥ ሶርያውያንን ከቂር አላወጣሁምን? አውጥቻለሁ።
ጽዮን ሆይ! ደስ ይበልሽ! ኢየሩሳሌም ሆይ! በደስታ እልል በይ! እነሆ ንጉሥሽ ትሑት ሆኖ፥ በአህያይቱ ማለትም በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ፥ በድል አድራጊነት ወደ አንቺ ይመጣል።
እርሱ ብቻ መድኃኒታችን ለሆነው አምላክ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከጥንት ጀምሮ፥ አሁንም፥ ለዘለዓለምም ክብርና ግርማ፥ ኀይልና ሥልጣንም ይሁን! አሜን።