Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 43:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 በውሃ ውስጥ በምታልፉበት ጊዜ እኔ ከእናንተ ጋር እሆናለሁ፤ በወንዞች መካከል በምታልፉበት ጊዜ አያሰጥሙአችሁም፤ በእሳትም ውስጥ በምታልፉበት ጊዜ አያቃጥላችሁም፤ ነበልባሉም ዐመድ አያደርጋችሁም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 በውሃ ውስጥ በምታልፍበት ጊዜ፣ ከአንተ ጋራ እሆናለሁ፤ ወንዙን ስትሻገረው፣ አያሰጥምህም፤ በእሳት ውስጥ ስትሄድ፣ አያቃጥልህም፤ ነበልባሉም አይፈጅህም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥ በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ አያሰምጡህም፤ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም፤ ነበልባሉም አይፈጅህም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 በውኃ ውስጥ ባለ​ፍህ ጊዜ ከአ​ንተ ጋር እሆ​ና​ለሁ፤ ወን​ዞ​ችም አያ​ሰ​ጥ​ሙ​ህም፤ በእ​ሳ​ትም ውስጥ በሄ​ድህ ጊዜ አት​ቃ​ጠ​ልም፤ ነበ​ል​ባ​ሉም አይ​ፈ​ጅ​ህም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥ በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ አያሰጥሙህም፥ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም፥ ነበልባሉም አይፈጅህም።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 43:2
40 Referencias Cruzadas  

ከስድስት ዐይነት የመቅሠፍት አደጋዎች ይታደግሃል፤ በሰባተኛውም ምንም ጒዳት አይደርስብህም።


በጣም ጨለማ በሆነ ሸለቆ በኩል ባልሄድም እንኳ አንተ ከእኔ ጋራ ስለ ሆንክ፥ ምንም ክፉ ነገር አልፈራም። ያንተ በትርና ምርኲዝ ያጽናኑኛል።


ስለዚህ በጭንቀት ሰዓት እያንዳንዱ ለአንተ ታማኝ ሰው ወደ አንተ ይጸልይ፤ ብርቱ የመከራ ጐርፍ በሚመጣበት ጊዜ እርሱን አይነካውም።


አምላክ ሆይ! ብር በእሳት ተፈትኖ እንደሚጠራ ፈተንከን።


ጠላቶቻችን በግፍ እንዲረግጡን አደረግህ፤ በእሳትና በጐርፍ መካከል አለፍን፤ አሁን ግን ብልጽግና ወደ መላበት ወደ ሰፊ ቦታ አመጣኸን።


በሚጠራኝም ጊዜ እሰማዋለሁ፤ በመከራው ጊዜ ከእርሱ ጋር እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ፤ አከብረዋለሁም።


እስራኤላውያን ግን ውሃው በግራና በቀኝ እንደ ግድግዳ ሆኖ ስለ ቆመላቸው በደረቅ ምድር ተሻገሩ።


እግዚአብሔርም መልሶ “አይዞህ እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ እኔ እንደ ላክኹህም ምልክት የሚሆንህ ይህ ነው፤ ሕዝቤን ከግብጽ በምታወጣበት ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ እኔን ታመልኩኛላችሁ” አለው።


የሠራዊት ጌታ አምላክ ነጐድጓድን፥ የመሬት መናወጥን፥ ታላቅ ድምፅን፥ ዐውሎ ነፋስን፥ ሞገድንና የሚባላ የእሳት ነበልባልን በጠላቶችሽ ላይ በመላክ አንቺን ይታደግሻል።


እነሆ፥ የእግዚአብሔር ኀይልና ግርማ ከሩቅ ይታያል፤ ነበልባልና ጢስ የቊጣው ምልክቶች ናቸው፤ በሚናገርበትም ጊዜ ቃሉ እንደ እሳት ይነዳል።


እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ! እኔ አምላክህ ነኝ፥ ተስፋ አትቊረጥ! እኔ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፤ ድል ነሺ በሆነ ክንዴ እደግፍሃለሁ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እንደ ትል ደካማ የሆንክ እስራኤል ሆይ! እኔ ስለምረዳህ አትፍራ፤ የምታደግህ የእስራኤል ቅዱስ እኔ ነኝ።


እኔ ከእናንተ ጋር ስለ ሆንኩ አትፍሩ፤ ከምሥራቅም ከምዕራብም እናንተንና ልጆቻችሁን ሰብስቤ አመጣለሁ።


አሁን እንደምትፈሩት የባቢሎንን ንጉሥ ከእንግዲህ ወዲያ አትፍሩት፤ እኔ ከእናንተ ጋር ስለ ሆንኩ ከእርሱ ኀይል እታደጋችኋለሁ፤


እኔ ከእናንተ ጋራ ስለ ሆንኩ አገልጋዮቼ እስራኤላውያን ሆይ! እናንተ አትፍሩ፤ እናንተ በሀገራቸው እንድትበታተኑ ያደረግኹባቸውን ሕዝቦች ሁሉ አጠፋለሁ፤ እናንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋችሁም፤ ሆኖም ለማረም እቀጣችኋለሁ፤ ሳልቀጣችሁ ግን አላልፍም፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


ሦስቱ ሰዎች ግን በጥብቅ እንደ ታሰሩ በእሳቱ ነበልባል ላይ ወደቁ።


የእግዚአብሔር መልእክተኛ የሆነው ሐጌ ለሕዝቡ “ ‘እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ’ ይላል እግዚአብሔር” ሲል የእግዚአብሔርን መልእክት አስተላለፈ።


እነርሱንም ወደ እሳት እጨምራቸዋለሁ፤ ብርም በእሳት እንደሚጠራ አጠራቸዋለሁ፤ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፤ ከዚያን በኋላ ወደ እኔ ይጸልያሉ፤ እኔም እመልስላቸዋለሁ። እኔ ‘ሕዝቤ’ ብዬ እጠራቸዋለሁ፤ እነርሱም ‘እግዚአብሔር አምላካችን’ ብለው ይጠሩኛል።”


የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ ትዕቢተኞችና ክፉ አድራጊዎች እንደ ገለባ በእሳት የሚቃጠሉበት ጊዜ እየመጣ ነው፤ የሚመጣውም ከእነርሱ ሥር፥ ወይም ቅርንጫፍ ሳያስቀር ሁሉንም ያቃጥላል።


“እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙም ‘ዐማኑኤል’ ተብሎ ይጠራል።” ዐማኑኤል ማለትም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው” ማለት ነው።


ነገር ግን መልእክቱ በእኔ አማካይነት በሙሉ እንዲነገርና አሕዛብ ሁሉ እንዲሰሙት ጌታ ከእኔ ጋር ሆኖ አበረታኝ፤ ከአንበሳም አፍ ድኛለሁ።


ጌታ ከአንተ ጋር ይሁን። የእግዚአብሔር ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።


እስራኤላውያን በደረቅ ምድር እንደሚሻገሩ ሆነው ቀይ ባሕርን የተሻገሩት በእምነት ነው፤ ግብጻውያን ግን እንዲሁ ለማድረግ በሞከሩ ጊዜ ሁሉም ሰጠሙ።


አንተ ኢያሱ፥ በምትኖርበት ዘመን ሁሉ አንተን ተቋቊሞ ድል የሚነሣህ ማንም አይኖርም፤ እኔ ከሙሴ ጋር እንደ ነበርኩ ከአንተም ጋር እሆናለሁ፤ ሁልጊዜም ከአንተ ጋር ነኝ፤ ከቶም አልተውህም፤


በምትሄድበት ሁሉ፥ እኔ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ስለምሆን አይዞህ! በርታ! አትፍራ! ብዬ አዝሃለሁ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos