ኢሳይያስ 32:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደስ የሚያሰኘው ለሙ መሬትና የወይን ቦታ ሁሉ ስለ ጠፋ ደረታችሁን እየደቃችሁ አልቅሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ ለሙ መሬት ደረታችሁን ምቱ፤ ስለ ፍሬያማው የወይን ተክል ዕዘኑ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ ለሙ እርሻ፥ ስለፍሬያማውም ወይን ደረታችሁን ድቁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ተወደደችዉ እርሻ ስለሚያፈራውም ወይን ደረታችሁን ድቁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለተወደደችውም እርሻ ስለሚያፈራውም ወይን ደረታችሁን ድቁ። |
የእሾኽ ቊጥቋጦና ኲርንችት በሕዝቤ ምድር ላይ በቅሎአል፤ ሕዝቦች በደስታ ይኖሩባቸው ስለ ነበሩት ቤቶችና በደስታ ተሞልታ ስለ ነበረችው ስለዚህች ከተማ አልቅሱ!
ከዚህም በላይ ከዓለም ምድር ሁሉ ውብ የሆነችውንና በማርና በወተት የበለጸገችውን ምድር እሰጣችኋለሁ ብዬ ቃል ገብቼላቸው ነበር። ከዚያ በኋላ ግን በበረሓ እያሉ ወደዚያ እንደማላስገባቸው አረጋግጬ ነገርኳቸው።
ከግብጽ ምድር አወጣኋቸው፤ ለእነርሱ የመረጥኩላቸው ምድር በማርና በወተት የበለጸገች ነበረች፤ እርስዋም ከዓለም ምድር ሁሉ ይበልጥ የተዋበች ነበረች፤ ወደዚያች ምድርም እንደማስገባቸው ቃል የገባሁላቸው በዚያን ጊዜ ነው።
ነነዌ ተዋረደች፤ ንግሥቲቱ ተማርካ ተወሰደች፤ ሴቶች አገልጋዮችዋ የርግብ ድምፅ የመሰለ የሐዘን ድምፅ ያሰማሉ፤ ደረታቸውንም እየመቱ ያለቅሳሉ።