ኢሳይያስ 27:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሆኖም የአትክልቱ ቦታ በእኔ ጥበቃ ከተማመነ እርሱ ወዳጄ ይሆናል፤ ከእኔም ጋር በሰላም ይኖራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አለዚያ ይምጡና መሸሸጊያቸው ያድርጉኝ፤ ከእኔ ጋራ ሰላም ይፍጠሩ፤ አዎን፤ ከእኔ ጋራ ሰላም ያድርጉ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህ ካልሆነ ግን ጉልበቴን ለእርዳታ ይያዝ፥ ከእኔ ጋር ሰላም ያድርግ፤ ከእኔ ጋር ሰላም ያድርግ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በውስጧ የሚኖሩ ይጮሃሉ፤ ከእርሱ ጋር ሰላምን እናድርግ፤ ከእርሱ ጋር ሰላምን እናድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወይም ጕልበቴን ይያዝ፥ ከእኔ ጋር ሰላም ያድርግ፥ ከእኔ ጋር ሰላም ያድርግ። |
በእርግጥ እግዚአብሔር መድኃኒቴ ነው፤ በእርሱ ስለምተማመን የሚያስፈራኝ የለም፤ እግዚአብሔር አምላክ ኀይሌና ብርታቴ ነው፤ እርሱም መድኃኒቴ ሆኖአል።
ለድኾች፥ ለመጻተኞችና ለችግረኞች በችግራቸው ጊዜ መጠጊያ ሆነህላቸዋል፤ ከዐውሎ ነፋስ የሚድኑበት ተገንና ከፀሐይ ቃጠሎ የሚጠለሉበት ጥላ ሆነህላቸዋል፤ የጨካኞች ምት የክረምት ወጀብ ግድግዳን እንደሚገፋ ያለ ነው።
ከአገልጋዬ በቀር ዕውር ማነው? ከምልከው መልእክተኛዬስ በቀር ደንቆሮ ማነው? ራሱን ለእኔ እንዳስገዛው ያለው ዕውር ማን ነው? ወይም እንደ እግዚአብሔር አገልጋይ ያለ ዕውር ማን ነው?
በኃጢአታችን ምክንያት ፊትህን ስላዞርክብንና ለበደላችንም ተገዢዎች እንድንሆን ስለ ተውከን ስምህን የሚጠራና አንተን ለማግኘት የሚጥር ማንም የለም።
“ኢየሩሳሌም! ኢየሩሳሌም ሆይ! አንቺ ነቢያትን የምትገድዪ፥ ወደ አንቺ የተላኩትንም መልእክተኞች በድንጋይ የምትወግሪ፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን በክንፎችዋ ሥር እንደምትሰበስብ፥ እኔም ስንት ጊዜ ልጆችሽን መሰብሰብ ፈለግኹ! አንቺና ሕዝብሽ ግን እምቢ አላችሁ።
በዚሁ ዐይነት እግዚአብሔር የማይለወጡትንና የማይዋሽባቸውን ሁለቱን ነገሮች፥ ማለትም ተስፋውንና መሐላውን ሰጥቶናል፤ በእነዚህም በሁለቱ ነገሮች አማካይነት በፊታችን ያለውን ተስፋ አጥብቀን መያዝ እንድንችል መጠጊያ ለማግኘት ወደ እርሱ የሸሸን እኛ ታላቅ መጽናናትን እናገኛለን።
የገባዖን ሰዎችም ሰፈሩን በጌልገላ አድርጎ ወደነበረው ወደ ኢያሱ እንዲህ ሲሉ መልእክት ላኩበት፦ “በተራራማው አገር የሚኖሩት የአሞራውያን ነገሥታት ሁሉ እኛን ሊወጉን ስለ ተባበሩብን እኛ አገልጋዮችህን ችላ አትበል! በቶሎ ወደ እኛ ወጥተህ እርዳንና አድነን!”