Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 27:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ይህ ካልሆነ ግን ጉልበቴን ለእርዳታ ይያዝ፥ ከእኔ ጋር ሰላም ያድርግ፤ ከእኔ ጋር ሰላም ያድርግ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 አለዚያ ይምጡና መሸሸጊያቸው ያድርጉኝ፤ ከእኔ ጋራ ሰላም ይፍጠሩ፤ አዎን፤ ከእኔ ጋራ ሰላም ያድርጉ።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ሆኖም የአትክልቱ ቦታ በእኔ ጥበቃ ከተማመነ እርሱ ወዳጄ ይሆናል፤ ከእኔም ጋር በሰላም ይኖራል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 በው​ስጧ የሚ​ኖሩ ይጮ​ሃሉ፤ ከእ​ርሱ ጋር ሰላ​ምን እና​ድ​ርግ፤ ከእ​ርሱ ጋር ሰላ​ምን እና​ድ​ርግ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ወይም ጕልበቴን ይያዝ፥ ከእኔ ጋር ሰላም ያድርግ፥ ከእኔ ጋር ሰላም ያድርግ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 27:5
22 Referencias Cruzadas  

የጨካኞችም ቁጣ እስትንፋስ ቅጥርን እንደሚመታ ዐውሎ ነፋስ በሆነ ጊዜ፥ ለድሀው መጠጊያ፥ ለችግረኛው በጭንቁ ጊዜ መሸሸጊያ፥ ከውሽንፍር መጠለያ፥ ከሙቀትም ጥላ ሆነሃል።


“እንግዲህ አሁንም ከእርሱ ጋር ተስማማ፥ ሰላምም ይኑርህ፥ በዚያም መልካምን ታገኛለህ።


ይሄውም እግዚአብሔር ሊዋሽ በማይቻል በሁለት በማይለወጥ ነገር፥ በፊታችን ያለውን ተስፋ ለመያዝ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ መጽናናት እንዲሆንልን ነው።


የከንፈሮችን ፍሬ እፈጥራለሁ፤ በሩቅም በቅርብም ላለው ሰላም ሰላም ይሁን፥ እፈውሰውማለሁ፥ ይላል ጌታ።


ይህን የሚያደርግ ሰው ይህንንም የሚይዝ የሰው ልጅ፥ እንዳያረክሰው ሰንበትንም የሚጠብቅ እጁንም ክፋት ከማድረግ የሚጠብቅ ብፁዕ ነው።


ስለ እኔም፦ በጌታ ዘንድ ብቻ ጽድቅና ኃይል አለ፥ ወደ እርሱም ሰዎች ይመጣሉ፥ በእርሱም ላይ የተቆጡ ሁሉ ያፍራሉ።


የገባዖንም ሰዎች ኢያሱ ወደ ሰፈረበት ወደ ጌልገላ ልከው እንዲህ አሉት፦ “ባርያዎችህን ለመርዳት እጅህን አትመልስ፤ በተራራማው አገር የሚኖሩ የአሞራውያን ነገሥታት ሁሉ ተሰብስበውብናልና ፈጥነህ ወደ እኛ ውጣ አድነንም እርዳንም።”


“አንቺስ ለሰላምሽ የሚሆነውን ምነው በዚህ ቀን ባወቅሽ ኖሮ! ነገር ግን አሁን ከዐይንሽ ተሰውሮአል።


ስምህንም የሚጠራ፥ አንተንም ሊይዝ የሚያስብ የለም፤ ፊትህንም ከእኛ ሰውረሃል፥ በኃጢአታችንም አጥፍተኸናል።


ካልሆነም ሌላው ገና ሩቅ ሳለ መልእክተኞች ልኮ ዕርቅ ይለምናል።


ኢየሩሳሌም! ኢየሩሳሌም! ነቢያትን የምትገድል፥ ወደ እርሷ የተላኩትንም የምትወግር፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን በክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን ለመሰብሰብ ስንት ጊዜ ፈለግሁ፤ እናንተ ግን አልፈለጋችሁም።


እነሆ፤ ጌታ መዳኛዬ ነው፤ እታመናለሁ፤ ደግሞም አልፈራም፤ ጌታ እግዚአብሔር ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ የመዳኔ ምክንያትም ሆኖአል።”


አቤቱ ጌታ፥ ሥራችንን ሁሉ ሠርተህልናልና ሰላምን ትሰጠናለህ።


ከአገልጋዬ በቀር ዕውር ማን ነው? እንደምልከው መልእክተኛዬስ ደንቆሮ የሆነ ማን ነው? እንደ ፍጹም ተገዢዬ ወይም እንደ ጌታ አገልጋይ ዕውር የሆነ ማን ነው?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios