ኢሳይያስ 23:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዘውድን ታቀዳጅ በነበረችው ከተማ፥ ልዑላን የሆኑና በዓለም የተከበሩ ነጋዴዎች በነበርዋት በጢሮስ ላይ ይህን ሁሉ ያቀደ ማነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም አክሊል በምታቀዳጀዋ፣ ነጋዴዎቿ መሳፍንት በሆኑ፣ በምድር የከበሩ ሻጮችና ለዋጮች በነበሯት፣ በጢሮስ ላይ ይህን ያሰበ ማን ነበር? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አክሊል በተቀዳጀች፥ ነጋዴዎችዋ መሳፍንት በሆኑ፥ በምድር የከበሩ ሻጮችና ለዋጮች በነበሯት፥ በጢሮስ ላይ ይህን ያሰበ ማን ነበር? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጢሮስ ላይ ይህን የመከረ ማን ነው? እርስዋ ከሁሉ የምትሻልና የምትበልጥ አይደለችምን? ነጋዴዎችዋ የከበሩ የምድር አለቆች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አክሊል ባስጫነች ከተማ በጢሮስ ላይ ይህን የወሰነ ማን ነው? ነጋዴዎችዋ አለቆች ናቸው፥ በእርስዋ የሚሸጡና የሚለወጡ የምድር ክቡራን ናቸው። |
አንተ ከአሦራውያን ባለሥልጣኖች የመጨረሻውን ዝቅተኛ መኰንን እንኳ ለመቋቋም የምትችል አይደለህም፤ ይህም ሆኖ ግብጻውያን ሠረገሎችንና ፈረሰኞችን ይልኩልኛል ብለህ ተስፋ ታደርጋለህ።
ሀብትሽ ይማረካል፤ የንግድ ዕቃሽ ይዘረፋል፤ ቅጥርሽ ይፈርሳል፤ የተዋቡ ቤቶችሽ ይፈራርሳሉ፤ ድንጋዮችሽ፥ ሳንቃዎችሽና ፍርስራሹ ወደ ባሕር ይጣላሉ።
የመብራት ብርሃን ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ አያበራም፤ የሙሽራውና የሙሽራይቱ ድምፅ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ አይሰማም፤ ነጋዴዎችሽ የዓለም ታላላቅ ሰዎች ነበሩ፤ በአስማትሽ ሕዝቦችን ሁሉ አሳስተሻል።
ስለዚህ መቅሠፍቶችዋ ሁሉ በአንድ ቀን ይደርሱባታል፤ ሞትና ሐዘን ራብም ይደርሱባታል፤ በእሳትም ትቃጠላለች፤ በእርስዋ ላይ የሚፈርድባት ጌታ አምላክ ብርቱ ነው።”