ይህም የሠራዊት አምላክ የወይን ቦታ የተባለው የእስራኤል ሕዝብ ነው፤ እርሱም የይሁዳ ሕዝብ ደስ የሚሰኝበት ተክል ነው። መልካም ሥራ እንዲሠሩ ተስፋ ያደርግ ነበር፤ በዚህ ፈንታ ነፍሰ ገዳዮች ሆኑ፤ ቅን ፍርድ ይሰጣሉ ብሎ ተስፋ ያደርግ ነበር፤ እነርሱ ግን ፍርድን በማጓደላቸው የሕዝቡ ጩኸት በዛ።
ሆሴዕ 10:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሐሰት መሐላ ቃል ኪዳን በመግባት ከንቱ ንግግር ይናገራሉ፤ ስለዚህ በእርሻ መሬት ውስጥ መርዘኛ አረም እንደሚበቅል በእነርሱም መካከል ክርክር ይስፋፋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከንቱ ተስፋ ይሰጣሉ፤ በሐሰት በመማል፣ ቃል ኪዳን ያደርጋሉ፤ ስለዚህም ፍርድ፣ በዕርሻ ውስጥ እንደሚገኝ መርዛማ ዐረም ይበቅላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የማይረባውን ቃላት ተናገሩ፤ በሐሰት መሐላ ቃል ኪዳን አደረጉ፤ ስለዚህ መርዛም አረም በእርሻ ትልሞች ላይ እንደሚበቅል መቅሠፍት በቀለባቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የማይረባውን የሐሰት ቃል ይናገራሉ፤ ቃል ኪዳንም ያደርጋሉ፤ ስለዚህ መርዛም ሣር በእርሻ ትልም ላይ እንደሚበቅል ፍርድ ይበቅልባቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የማይረባውን ቃል ይናገራሉ፥ ቃል ኪዳን በገቡ ጊዜ በሐሰት ይምላሉ፥ ስለዚህ መርዛም ሣር በእርሻ ትልም ላይ እንደሚበቅል መቅሠፍት ይበቅልባቸዋል። |
ይህም የሠራዊት አምላክ የወይን ቦታ የተባለው የእስራኤል ሕዝብ ነው፤ እርሱም የይሁዳ ሕዝብ ደስ የሚሰኝበት ተክል ነው። መልካም ሥራ እንዲሠሩ ተስፋ ያደርግ ነበር፤ በዚህ ፈንታ ነፍሰ ገዳዮች ሆኑ፤ ቅን ፍርድ ይሰጣሉ ብሎ ተስፋ ያደርግ ነበር፤ እነርሱ ግን ፍርድን በማጓደላቸው የሕዝቡ ጩኸት በዛ።
ፈረሰኛ በቋጥኝ ላይ ሊጋልብ ይችላልን? ገበሬስ በባሕር ላይ በሬ ጠምዶ ማረስ ይችላልን? እናንተ ግን ፍርድን ወደ መርዝ ለወጣችሁ፤ እውነትንም እንደ ሬት መራራ አደረጋችሁ።
በዚህ ከቆማችሁት መካከል ማንም ወንድ ወይም ሴት፥ ቤተሰብ ወይም ነገድ ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ፈቀቅ በማለት የሌሎችን ሕዝቦች አማልክት የሚከተል እንዳይኖር ተጠንቀቁ፤ በመካከላችሁ እንደዚህ ያለ መርዘኛና መራራ የሆነ ሥራ የሚሠራ አይኑር፤
እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አንተ በቅርብ ጊዜ እንደ ቀድሞ አባቶችህ ትሞታለህ፤ ከዚያ በኋላ ይህ ሕዝብ ከእርሱ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን ያፈርሳል። እኔንም በመተው በሚወርሰው ምድር የሚገኙትን ጣዖቶች ያመልካል።
ይህም በሚሆንበት ጊዜ እኔ በእነርሱ ላይ ተቈጥቼ እለያቸዋለሁ፤ ፊቴን ከእነርሱ እሰውራለሁ፤ እነርሱም ይደመሰሳሉ፤ በእነርሱም ላይ ብዙ አሠቃቂ መቅሠፍት ይመጣባቸዋል፤ በዚያን ጊዜ፥ ‘ይህ ችግር የመጣብን አምላካችን በመካከላችን ስለሌለ አይደለምን?’ ይላሉ።
ከእናንተ ማንም የእግዚአብሔር ጸጋ እንዳይጐድልበት ተጠንቀቁ፤ እንዲሁም ምንም መራራ ፍሬ የሚያፈራ ሥር በመካከላችሁ እንዳይበቅልና እንዳያስቸግራችሁ ብዙዎችንም እንዳያረክስ ተጠንቀቁ።