ዕብራውያን 4:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእርሱ ሥራ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተጠናቀቀ ቢሆንም እንኳ፦ “እኔ ወደምሰጣቸው የዕረፍት ቦታ ከቶ አይገቡም ብዬ በቊጣዬ ምዬአለሁ” እንዳለው አሁንም እኛ የምናምነው ወደዚያ እግዚአብሔር ወደሚሰጠን የዕረፍት ቦታ እንገባለን፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኛ ያመንነው ግን ወደዚያ ዕረፍት እንገባለን፤ እግዚአብሔርም፣ “ስለዚህ በቍጣዬ እንዲህ ብዬ ማልሁ፤ ‘ፈጽሞ ወደ ዕረፍቴ አይገቡም’ ” ብሏል። ይሁን እንጂ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የርሱ ሥራ ተከናውኗል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሥራው ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ምንም እንኳ ቢፈጸም “እንዲህ ‘ወደ ዕረፍቴ አይገቡም፤’ ብዬ በቁጣዬ ማልሁ፤” እንዳለ፥ እኛስ ያመንን ወደ ዕረፍቱ እንገባለን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሥራዉ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ምንም እንኳ ቢፈጸም፥ “እንግዲህ ወደ ዕረፍቴ አይገቡም ብዬ በቍጣዬ ማልሁ” እንዳለ እኛስ ያመንን ወደ ዕረፍቱ እንገባለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሥራው ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ምንም እንኳ ቢፈጸም፦ እንዲህ፦ ወደ ዕረፍቴ አይገቡም ብዬ በቁጣዬ ማልሁ እንዳለ፥ እኛስ ያመንን ወደ ዕረፍቱ እንገባለን። |
በስድስት ቀን እግዚአብሔር ሰማይን፥ ምድርን፥ ባሕርንና በእነርሱ ውስጥ ያሉትን ነገሮች ሁሉ ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን ዐረፈ፤ ስለዚህም እግዚአብሔር ሰባተኛውን ቀን ባረከው፤ ቀደሰውም።
እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንዲህ ይላል፦ “በየጐዳናው ቆማችሁ ተመልከቱ፤ ጥንታዊና መልካም የሆነችው መንገድ የትኛዋ እንደ ሆነች ጠይቃችሁ ተረዱ፤ ባገኛችኋትም ጊዜ በእርስዋ ሂዱ፤ በሰላምም ትኖራላችሁ።” ሕዝቡ ግን “በእርስዋ አንሄድም!” አሉ።
ዐመፀኞችንና የበደሉኝን ከመካከላችሁ አስወግዳለሁ፤ አሁን ከሚኖሩባቸው አገሮች አወጣቸዋለሁ፤ ነገር ግን ወደ እስራኤል ምድር እንዲመለሱ ከቶ አልፈቅድላቸውም፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።”
ይህም የሆነበት ምክንያት በነቢይ እንዲህ ተብሎ የተጻፈው እንዲፈጸም ነው፦ “ንግግሬን በምሳሌ እገልጣለሁ፤ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተሰወረውን እናገራለሁ።”
በዚያን ጊዜ ንጉሡ በቀኙ በኩል ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፦ ‘እናንተ አባቴ የባረካችሁ! ኑ! ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ!
እንዲህማ ቢሆን ኖሮ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ብዙ ጊዜ መከራ መቀበል ባስፈለገው ነበር፤ አሁን ግን በዘመናት መጨረሻ ኃጢአትን ለማስወገድ ራሱን መሥዋዕት በማድረግ አንዴ በማያዳግም ሁኔታ ተገልጦአል።