ዕብራውያን 13:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአይሁድ የካህናት አለቃ የኃጢአት ይቅርታን የሚያስገኘውን የእንስሳት ደም ይዞ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ይገባል፤ የእንስሳቱ በድን ግን ከሰፈሩ ውጪ ይቃጠላል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሊቀ ካህናቱ ስለ ኀጢአት ስርየት የሚሆነውን የእንስሳት ደም ይዞ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ይገባል፤ የእንስሳቱ ሥጋ ግን ከሰፈር ውጭ ይቃጠላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሊቀ ካህናት ስለ ኃጢአት የእንስሶችን ደም ወደ ቅድስት ያቀርባል፤ ሥጋቸው ግን ከሰፈሩ ውጭ ይቃጠላል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሊቀ ካህናቱ የሚሠዉትን እንስሳ ደም ስለ ኀጢአት ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ያቀርብ ነበርና፤ ሥጋውንም ከሰፈር ውጭ ያቃጥሉት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሊቀ ካህናት ስለ ኃጢአት ወደ ቅድስት የእንስሶችን ደም ያቀርባልና፤ ሥጋቸው ግን ከሰፈሩ ውጭ ይቃጠላል። |
ለኃጢአት ስርየት መሥዋዕት ሆኖ የቀረበውንም ኰርማ ወስደህ ለቤተ መቅደሱ ከተከለለው የተቀደሰ ቦታ ውጪ ለዚህ በተወሰነው ስፍራ ታቃጥለዋለህ።
ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት ሆነው የቀረቡትና ኃጢአትን ለማስተስረይ ደማቸው ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ገብቶ የነበረው ኰርማና ፍየልም ከሰፈር ወደ ውጪ ተወስደው በእሳት ይቃጠሉ፤ እንዲሁም ቆዳቸው፥ ሥጋቸውና የሆድ ዕቃቸው በሙሉ ይቃጠል።
ልጆቹም ደሙን ወደ እርሱ አመጡለት፤ እርሱም ደሙን በጣቱ እያጠቀሰ በመሠዊያው ላይ ያሉትን ጒጦች ቀባ፤ የተረፈውንም ደም በመሠዊያው ሥር አፈሰሰ፤