ዘፍጥረት 7:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የፈጠርኩትን ሕያው ፍጡር ሁሉ ከምድር ገጽ ላይ ለማጥፋት ከሰባት ቀን በኋላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ሙሉ ዝናብ አዘንባለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሰባት ቀን በኋላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በምድር ላይ ዝናብ አዘንባለሁ፤ የፈጠርሁትንም ሕያው ፍጡር ሁሉ ከምድር ገጽ አጠፋለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የፈጠርሁትንም ፍጥረት ሁሉ ከምድር ላይ ለማጥፋት ከሰባት ቀን በኋላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በምድር ላይ ዝናብ አዘንባለሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሰባት ቀን በኋላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በምድር ላይ ዝናብ አዘንባለሁና፤ የፈጠርሁትንም ፍጥረት ሁሉ ከምድር ሁሉ ላይ አጠፋለሁና።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሰባት ቀን በኍላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በምድር ላይ ዝናብ አዘንባለሁና፤ የፈጠርሁትንም ፍጥረት ሁሉ ከምድር ላይ አጠፉለሁና። |
እግዚአብሔር ኖኅን እንዲህ አለው፦ “የሰውን ዘር ለማጥፋት ወስኛለሁ፤ ምድር በሰዎች የዐመፅ ሥራ ስለ ተሞላች ሰዎችን ከምድር ጋር አጠፋቸዋለሁ፤
እነሆ፥ ከሰማይ በታች ሕይወት ያለውን ነገር ሁሉ ከምድር ላይ ለማጥፋት የጥፋት ውሃ አመጣለሁ፤ በምድር ላይ ያለ ሕያው ፍጥረት ሁሉ ይጠፋል።
እግዚአብሔርም “ሕይወት ሰጪ የሆነ መንፈሴ ከሰዎች ጋር ለዘለዓለም አይኖርም፤ ሰዎች ሟቾች ስለ ሆኑ ከእንግዲህ ወዲያ ከ 120 ዓመት የበለጠ አይኖሩም” አለ።
በዚህ ምክንያት እግዚአብሔር “እነርሱን በመፍጠሬ አዝኛለሁ፤ ስለዚህ እነዚህን የፈጠርኳቸውን ሰዎች፥ እንስሶችን፥ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶችንና ወፎችንም ጭምር ከምድር ላይ አጠፋለሁ” አለ።
ከያንዳንዱ ዐይነት ወፍ ወንድና ሴት ሰባት ወንድ ሰባት ሴት አስገባ፤ ይህንንም የምታደርገው እያንዳንዱ ዐይነት እንስሳና ወፍ በሕይወት እንዲኖርና በምድር ላይ ለዘር እንዲተርፍ ነው።
ስለዚህም እግዚአብሔር ‘አንተን ከምድረ ገጽ አስወግድሃለሁ ይህ ሕዝብ በእኔ በአምላካቸው ላይ እንዲያምፁ በማድረግህ ምክንያት ይህ ዓመት ከመፈጸሙ በፊት ትሞታለህ’ ይላል።”
አዝመራችሁ ከመድረሱ ከሦስት ወር በፊት ዝናብ እንዲቋረጥ አደረግሁ፤ በአንድ ከተማ ሲዘንብ በሌላው ከተማ እንዳይዘንብ አደረግሁ፤ ለአንዱ እርሻ ሲዘንብለት ሌላው እርሻ ዝናብ አጥቶ ደረቀ።
ድል የሚነሣ እንደ እነርሱ ነጭ ልብስ ይለብሳል፤ ስሙን በአባቴና በመላእክቱም ፊት አስታውቅለታለሁ፤ የሕያዋን ስም ከሚመዘገብበት ከሕይወት መጽሐፍ አልደመስሰውም።