ዘፍጥረት 7:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍጥረት ሁሉ ወንድና ሴት ሆነው ወደ መርከቡ የገቡት እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ነው፤ ከዚህ ቀጥሎ እግዚአብሔር ከኖኅ በስተኋላ የመርከቡን በር ዘጋ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሕያዋንም ፍጥረታት ሁሉ እግዚአብሔር ኖኅን ባዘዘው መሠረት ተባዕትና እንስት እየሆኑ ገቡ፤ ከዚያም እግዚአብሔር ከውጭ ዘጋበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍጥረት ሁሉ ወንድና ሴት ሆነው ወደ መርከቡ የገቡት እግዚአብሔር እንዳዘዘው ገቡ፤ ጌታም በስተ ኋላው ዘጋበት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሥጋ ካለው ሁሉ የገቡትም ተባትና እንስት እግዚአብሔር ኖኅን እንዳዘዘው ገቡ፤ እግዚአብሔር አምላክም መርከብዋን በስተውጭ ዘጋት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሥጋ ካለው ሁሉ የገቡትም ተባትና እንስት እግዚአብሔርም በስተ ኋላው ዘጋበት። |
ሞኞቹ ልጃገረዶች፥ ዘይት ለመግዛት በሄዱበት ወቅት ሙሽራው መጣ። ተዘጋጅተው የነበሩትም ልጃገረዶች ከሙሽራው ጋር ወደ ሠርጉ ግብዣ አዳራሽ ገቡ፤ በሩም ተዘጋ።
የቤቱ ጌታ ተነሥቶ በሩን ይዘጋዋል፤ እናንተም በደጅ ቆማችሁ በሩን በማንኳኳት፥ ‘ጌታ ሆይ! እባክህ ክፈትልን!’ ማለት ትጀምራላችሁ፤ እርሱም ‘ከየት እንደ መጣችሁ አላውቅም!’ ሲል ይመልስላችኋል።