ዘፍጥረት 6:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በምድር ላይ ያሉ ሰዎች ሁሉ ምን ያኽል ዐመፀኞች እንደ ሆኑና ሐሳባቸውም ዘወትር ክፋት ብቻ እንደ ሆነ ተመለከተ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር አምላክ የሰው ዐመፅ በምድር ላይ የበዛና የልቡም ሐሳብ ዘወትር ወደ ክፋት ብቻ ያዘነበለ መሆኑን ተመለከተ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም የሰው ክፋት በምድር ላይ እንደ በዛ፥ የልቡ አሳብ ምኞትም ሁልጊዜ ፈጽሞ ክፉ እንደሆነ አየ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም የሰዎች ክፉ ሥራ በምድር ላይ እንደበዛ፥ የልባቸው ዐሳብ ምኞትም ሁል ጊዜ ፈጽሞ ክፉ እንደሆነ አየ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም የሰው ክፉት በምድር ላይ እንደ በዛ፤ የልቡ አሳብ ምኞትም ሁልጊዜ ፈጽሞ ክፉ እንድ ሆነ አየ። |
የመሥዋዕቱም መዓዛ እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው፤ በሐሳቡም እንዲህ አለ፥ ገና ከሕፃንነቱ ጊዜ ጀምሮ የሰው ሐሳብ ክፉ መሆኑን ስለማውቅ፤ “ሰው በሚፈጽመው በደል ሁሉ ከእንግዲህ ወዲህ ምድርን አልረግምም፤ በአሁኑ ጊዜ እንዳደረግሁት ሕይወት ያለውን ፍጥረት ሁሉ ከእንግዲህ ወዲህ ከቶ አላጠፋም።
የሁሉም ዕድል ፈንታው አንድ ዐይነት ነው፤ ይህም በዓለም እንደሚደረገው እንደማንኛውም ነገር ሁሉ እጅግ የከፋ ነው፤ ሰዎችም በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ አእምሮአቸው በክፋትና በእብደት የተሞላ ሆኖ በመጨረሻ ይሞታሉ።
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ “የእስራኤል መሪዎች በየራሳቸው ጣዖት ቤት በጨለማ ሆነው እግዚአብሔር አያየንም! ምድሪቱንም ትቶአታል በማለት የሚያደርጉትን ታያለህን?” አለኝ።
እንደዚህ ያለው ሰው የዚህን ርግማን ቃላት ሰምቶ ምንም እንኳ በራሴ መንገድ ብቀጥል እኔ እድናለሁ ብሎ በልቡ ቢያስብ በደጎችና በክፉዎች ሰዎች ላይ ጥፋትን ያመጣል።
እኛም ከዚህ በፊት ሞኞች፥ የማንታዘዝ እምቢተኞች፥ መንገዳችንን የሳትን ተላላዎች፥ ለልዩ ልዩ ፍትወትና ሥጋዊ ደስታ የተገዛን፥ በተንኰልና በምቀኝነት የምንኖር፥ የተጠላንና እርስ በርሳችንም የምንጣላ ነበርን።
እነዚህ በወህኒ ቤት የነበሩ መናፍስት ቀድሞ በኖኅ ዘመን መርከብ ሲዘጋጅ እግዚአብሔር በትዕግሥት ሲጠብቃቸው ሳለ አንታዘዝም ያሉ ናቸው። በዚያ መርከብ ውስጥ ገብተው በውሃ አማካይነት የዳኑት ቊጥራቸው ስምንት የሆነ ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው።