ይህም የሚከማቸው እህል በግብጽ ምድር ላይ ወደፊት በሚመጡት ሰባት የራብ ዓመቶች ለአገሪቱ መጠባበቂያ ይሆናል፤ በዚህ ሁኔታ አገሪቱ በራብ ከመጐዳት ትድናለች።”
ዘፍጥረት 47:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኛና ምድራችን በፊትህ እንጥፋን? እኛንና መሬታችንን ገዝተህ እህል ስጠን፤ እኛ የንጉሡ ባሪያዎች እንሆናለን፤ መሬታችንም የእርሱ ይሁን፤ በልተን በሕይወት እንድንኖር እህል ስጠን፤ በመሬታችን ላይ የምንዘራውም ዘር ስጠን።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታዲያ፣ እያየኸን እንዴት እንለቅ? መሬታችንስ ለምን ጠፍ ሆኖ ይቅር? እኛንና መሬታችንን ውሰድና በለውጡ እህል ስጠን፤ እኛ የፈርዖን ገባሮች እንሁን፤ መሬታችንም የርሱ ርስት ይሁን፤ እኛም እንዳንሞት መሬታችንም ጠፍ ሆኖ እንዳይቀር የምንዘራው ዘር ስጠን።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኛ በፈትህ ስለምን እንሞታለን? ምድራችንስ ስለምን ትጠፋለች? እኛንም ምድራችንንም በእህል ግዛን፥ እኛም ለፈርዖን ባርያዎች እንሁን፥ ምድራችንም ለእርሱ ትሁን፥ እኛ እንድንድን እንዳንሞትም ምድራችንም እንዳትጠፋ ዘር ስጠን።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ እኛ በፊትህ እንዳንሞት፥ ምድራችንም እንዳትጠፋ፥ እኛንም፥ ምድራችንንም በእህል ግዛን፤ እኛም ለፈርዖን አገልጋዮች እንሁን፤ ምድራችንም ለእርሱ ትሁን፤ እኛ እንድንድን፥ እንዳንሞትም፥ ምድራችንም እንዳትጠፋ እንዘራ ዘንድ ዘር ስጠን።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምድራችንስ ስለ ምን ትጠፋለች? እኛንም ምድራችንንም በእህል ግዛን እኛም ለፈርዖን ባሪያዎች እንሁን ምድራችንም ለእርሱ ትሁን እኝ እንድንድን እንዳንሞትም ምድራችንም እንዳትጠፋ ዘር ስጠን። |
ይህም የሚከማቸው እህል በግብጽ ምድር ላይ ወደፊት በሚመጡት ሰባት የራብ ዓመቶች ለአገሪቱ መጠባበቂያ ይሆናል፤ በዚህ ሁኔታ አገሪቱ በራብ ከመጐዳት ትድናለች።”
በዚህ ሁኔታ የግብጽና የከነዓን ሕዝቦች ገንዘባቸውን በእህል ሸመታ ስለ ጨረሱ፥ ግብጻውያን ወደ ዮሴፍ ተሰብስበው መጥተው “የምንመገበው እህል ስጠን! ገንዘባችንን ስለ ጨረስን በራብ ማለቃችን ነው!” አሉት።
በሚቀጥለውም ዓመት ወደ እርሱ መጡና እንዲህ አሉት፤ “ጌታችን ሆይ! ከአንተ የምንሰውረው ነገር የለም፤ ገንዘባችን ሁሉ አልቆአል፤ ከብቶቻችንንም ለአንተ አስረክበናል፤ እንግዲህ ለጌታችን የምንሰጠው ከሰውነታችንና ከመሬታችን በቀር ሌላ ምንም ነገር የለንም።
ዮሴፍ በግብጽ ያለውን መሬት ሁሉ ለንጉሡ ገዛ፤ ከራቡ ጽናት የተነሣ ግብጻውያን ሁሉ መሬታቸውን መሸጥ ግድ ሆነባቸው፤ በዚህ ዐይነት መሬት ሁሉ የንጉሡ ንብረት ሆነ።
ሕዝብዋ ምግብ ማግኘት ፈልገው ይቃትታሉ፤ በሕይወት ለመኖር ሲሉ ሀብታቸውን ሁሉ በምግብ ይለውጣሉ፤ የኢየሩሳሌም ሕዝብ “እግዚአብሔር ሆይ! ተመልከተን! ውርደታችንን ሁሉ እይልን!” እያሉ ይጮኻሉ።