ዘፍጥረት 46:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የብንያም ልጆች፦ ቤላዕ፥ ቤኬር፥ አሽቤል፥ ጌራ፥ ናዕማን፥ ኤሒ፥ ሮሽ፥ ሙፊም፥ ሑፊምና አረድ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የብንያም ልጆች፦ ቤላ፣ ቤኬር፣ አስቤል፣ ጌራ፣ ናዕማን፣ አኪ፣ ሮስ፣ ማንፌን ሑፊምና አርድ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የብንያም ልጆች፦ ቤላዕ፥ ቤኬር፥ አሽቤል፥ ጌራ፥ ናዕማን፥ ኤሒ፥ ሮሽ፥ ሙፊም፥ ሑፊምና አረድ ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የብንያምም ልጆች፤ ቤላ፥ ቦኮር፥ አስቤር፤ የቤላ ልጆችም፤ ጌራ፥ ኖሔማን፥ አሒ፥ ሮስ፥ ማንፌን፥ ሑፈም፤ ጌራም አራድን ወለደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የብንያም ልጆች ቤላ፥ ቤኬር፥ አስቤል የቤላ ልጆችም ጌራ ናዕማን አኪ ሮስ፥ ማንፌን፥ ሑፊም ጌራም አርድን ወለደ። |
በዚያን ጊዜ ሼባዕ ተብሎ የሚጠራ ጠባዩ የተበላሸ የማይረባ አንድ ሰው በጌልገላ ይኖር ነበር፤ እርሱም ትውልዱ ከብንያም ነገድ ሲሆን አባቱ ቢክሪ ይባላል፤ ይህም ሼባዕ እምቢልታ ነፍቶ “ከዳዊት ጋር ምንም ድርሻ የለንም! ከእሴይ ልጅ ጋር ምንም ዕድል ፈንታ የለንም! የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! እያንዳንድህ ወደ ቤትህ ግባ!” ሲል ድምፁን ከፍ አድርጎ ተናገረ።
ስለ ብንያምም ነገድ እንዲህ አለ፦ “እግዚአብሔር የሚወደው ያለ ስጋት ይረፍ፤ ኀያሉ አምላክ ቀኑን ይጠብቀዋል። በእግዚአብሔር ጥበቃም ሥር ይኖራል።”