ኑ እንግደለውና ከእነዚህ ጒድጓዶች በአንደኛው ውስጥ እንጣለው፤ ከዚህ በኋላ ‘ክፉ አውሬ በላው’ ብለን ማመኻኘት እንችላለን፤ በዚህ ዐይነት የሕልሙን መጨረሻ እናያለን” አሉ።
ዘፍጥረት 45:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮሴፍ ወንድሞቹን “እኔ ዮሴፍ ነኝ፤ አባቴ እስከ አሁን በሕይወት አለን?” አላቸው። ወንድሞቹ የተናገረውን በሰሙ ጊዜ እጅግ ደነገጡ፤ መልስ መስጠትም ተሳናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮሴፍም ወንድሞቹን፣ “እኔ ዮሴፍ ነኝ፤ ለመሆኑ አባቴ እስካሁን በሕይወት አለ?” ሲል ጠየቃቸው። ወንድሞቹ ግን በፊቱ ተደናግጠው ስለ ነበር መልስ ሊሰጡት አልቻሉም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮሴፍም ለወንድሞቹ “እኔ ዮሴፍ ነኝ፥ አባቴ እስከ አሁን በሕይወቱ አለን?” አለ። ወንድሞቹም፥ በፊቱ ደንግጠው ነበርና፥ ሊመልሱለት አልቻሉም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮሴፍም ለወንድሞቹ፥ “እኔ ወንድማችሁ ዮሴፍ ነኝ፤ አባቴ እስከ አሁን በሕይወቱ ነውን?” አላቸው። ወንድሞቹም ይመልሱለት ዘንድ አልቻሉም፤ ደንግጠው ነበርና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮሴፍም ለወንድሞቹ፦ እኔ ዮሴፍ ነኝ አባቴ እስከ አሁን በሕይወቱ ነውን? አለ። ወንድሞቹም ይመጠው ነበርና። |
ኑ እንግደለውና ከእነዚህ ጒድጓዶች በአንደኛው ውስጥ እንጣለው፤ ከዚህ በኋላ ‘ክፉ አውሬ በላው’ ብለን ማመኻኘት እንችላለን፤ በዚህ ዐይነት የሕልሙን መጨረሻ እናያለን” አሉ።
እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ “በእርግጥ በወንድማችን ላይ ስላደረስነው በደል ተገቢውን ቅጣት በመቀበል ላይ ነን፤ ምሕረት እንድናደርግለት ተጨንቆ ሲለምነን ልመናውን አልተቀበልንም ነበር፤ በእኛም ላይ ይህ ጭንቀት ሊደርስብን የቻለው በዚህ ምክንያት ነው።”
ሮቤልም “እኔ በልጁ ላይ ጒዳት እንዳታደርሱ ነግሬአችሁ ነበር፤ ነገር ግን አልሰማችሁኝም፤ እነሆ፥ እርሱን በመግደላችን በቀሉን እየተቀበልን ነው” አላቸው።
“በዚያን ጊዜ በዳዊት ዘሮችና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ላይ የርኅራኄና የጸሎት መንፈስ እሞላለሁ፤ ይህንንም የማደርገው እነርሱ ለአንድያ ልጅና ለበኲር ልጅ እንደሚለቀስ ለወጉት ምርር ብለው እንዲያለቅሱለት ነው።
እነሆ በደመና ይመጣል፤ የወጉት ሰዎች እንኳ ሳይቀሩ ሰው ሁሉ ያየዋል፤ የምድርም ሕዝቦች ሁሉ በእርሱ ምክንያት ያለቅሳሉ፤ ይህ ነገር እውነት ነው፤ አሜን።