ዘፍጥረት 43:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ወንድማችንን ይዘን እንድንሄድ ከፈቀድክልን ሄደን እህል እንሸምትልሃለን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንድማችን ከእኛ ጋራ እንዲወርድ ከፈቀድህ ወደዚያ ሄደን እህል እንሸምትልሃለን፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድማችን ከእኛ ጋር እንዲወርድ ከፈቀድህ ወደዚያ ሄደን እህል እንሸምትልሃለን፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድማችንን ከእኛ ጋር ብትልከው እንወርዳለን፤ እህልም እንሸምትልሃልን፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድማችንን ከእና ጋር ብትሰድደው እንወርዳለን እህልም እንሸምትልሃለን ባትሰድደው ግን አንሄድም፤ |
እኛም ‘ታናሽ ወንድማችን ከእኛ ጋር ካልሆነ በሰውየው ፊት መቅረብ አንችልም፤ ስለዚህ ወደዚያ መሄድ የምንችለው ታናሽ ወንድማችን ከእኛ ጋር የሄደ እንደሆን ብቻ ነው’ አልነው።