እንዲህም አሉ፦ “ኑ አንድ ከተማ እንመሥርት፤ በዚያም ጫፉ እስከ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ላይ እንዳንበታተን ስማችንን እናስጠራ።”
ዘፍጥረት 42:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን “ጒዳት ይደርስበታል” ብሎ ስለ ፈራ ያዕቆብ ከዮሴፍ ጋር ከአንድ እናት የወለደውን ልጁን ብንያምን ከወንድሞቹ ጋር ወደ ግብጽ አላከውም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ያዕቆብ የዮሴፍን ወንድም ብንያምን፣ ክፉ ነገር ይደርስበታል በሚል ፍርሀት ከወንድሞቹ ጋራ አልላከውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ያዕቆብ የዮሴፍን ወንድም ብንያምን፥ ክፉ ነገር ይደርስበታል በሚል ፍርሀት ከወንድሞቹ ጋር አላከውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዮሴፍን ወንድም ብንያምን ግን ያዕቆብ ከወንድሞቹ ጋር አልሰደደውም፥ “ምናልባት ክፉ እንዳያገኘው” ብሎአልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዮሴፍ ወንድም ብንያምን ግን ያዕቆብ ከወንድሞቹ ጋር አልሰደደውም፦ ምናልባት ክፋ እንዳያግኘው ብሎአልና። |
እንዲህም አሉ፦ “ኑ አንድ ከተማ እንመሥርት፤ በዚያም ጫፉ እስከ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ላይ እንዳንበታተን ስማችንን እናስጠራ።”
እግዚአብሔር አምላክም እንዲህ አለ፦ “እነሆ፥ አዳም ክፉንና ደግን በማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ፤ አሁንም እጁን ዘርግቶ ከሕይወት ዛፍ ወስዶ በመብላት ለዘለዓለም እንዲኖር አይገባውም።”
ያዕቆብም “ምንም ቢሆን ከእናንተ ጋር አይሄድም፤ ወንድሙ ሞቶአል፤ የቀረው እርሱ ብቻ ነው፤ በመንገድ አንድ ጒዳት ቢደርስበት በእርጅናዬ ዘመን በመሪር ሐዘን ወደ መቃብር እንድወርድ ታደርጉኛላችሁ” አላቸው።
ብንያምንና ሌላውንም ወንድማችሁን መልሶ እንዲሰጣችሁ ሁሉን የሚችል አምላክ የዚያን ሰው ልብ ያራራላችሁ። እኔ በበኩሌ ልጆቼን ካጣሁ፥ ባዶ እጄን መቅረቴ ነው።”
ዮሴፍ የእናቱ ልጅ የሆነውን ወንድሙን ብንያምን ባየው ጊዜ “ ‘ታናሽ ወንድም አለን’ ብላችሁ ነግራችሁኝ ነበር፤ ይህ እርሱ ነውን?” አለና “ልጄ፥ እግዚአብሔር ይባርክህ” አለው።