ዘፍጥረት 40:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእንጀራ ቤት ኀላፊውን ግን እንዲሰቀል አደረገው፤ ሁሉም ነገር ዮሴፍ የእያንዳንዳቸውን ሕልም እንደ ተረጐመው ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእንጀራ ቤት አዛዡን ግን ልክ ዮሴፍ እንደ ተረጐመላቸው ሰቀለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእንጀራ ቤት አዛዡን ግን ልክ ዮሴፍ እንደ ተረጐመላቸው ሰቀለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእንጀራ አበዛዎቹንም አለቃ በዕንጨት ላይ ሰቀለው፤ ዮሴፍ እንደ ተረጐመላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእንጀራ አበዛዎቹንም አለቃ ሰቀለው ዮሴፍ እንደተረጎመላቸው። |
እነርሱም “እያንዳንዳችን ሕልም አየን፤ ነገር ግን የእያንዳንዳችንን ሕልም የሚተረጒም ማንም የለም” አሉት። ዮሴፍም “ሕልም የመተርጐም ችሎታ የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው፤ ስለዚህ የእያንዳንዳችሁን ሕልም ንገሩኝ” አላቸው።
ሕልም ያለመ ነቢይ ቢኖር ሕልሙን ብቻ ይናገር፤ ቃሌን የሰማ ነቢይ ግን ያንኑ ቃል በታማኝነት ይናገር፤ ገለባ ከስንዴ ጋር ምን ግንኙነት አለው?
ይህም ምሥጢር ለእኔ የተገለጠልኝ ከሌሎች ሰዎች ይልቅ ጥበበኛ ስለ ሆንኩ አይደለም፤ ነገር ግን አንተ የሕልሙን ትርጒም እንድታውቅና በአእምሮህም ውስጥ የተመላለሰውን ሐሳብ መረዳት እንድትችል ነው።
እርሱ ሕልምን በመተርጐም፥ እንቆቅልሽን በመፍታትና የተሰወረውን ምሥጢር ገልጦ በማስረዳት ልዩ ችሎታ ያለው ጥበበኛና ብልኅ ሰው ነው፤ ስለዚህ ያንን አባትህ ናቡከደነፆር ‘ብልጣሶር’ ብሎ የሠየመውን ዳንኤልን አስጠራ፤ እርሱ ይህን ሁሉ ነገር ተርጒሞ ያስረዳሃል።”