ዘፍጥረት 38:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዔር በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሰው ስለ ነበረ፥ እግዚአብሔር በሞት ቀሠፈው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የይሁዳ የበኵር ልጅ ዔር ግን በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነበር፤ እግዚአብሔርም ቀሠፈው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የይሁዳ የበኩር ልጅ ዔር ግን በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነበር፤ ጌታም ቀሠፈው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የይሁዳም የበኵር ልጅ ዔር በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነበረ፤ እግዚአብሔርም ቀሠፈው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የይሁዳም የበኵር ልጅ ዔር በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነበረ፤ እግዚአብሔር ቀሠፈው። |
የይሁዳ ልጆች፦ ዔር፥ ኦናን፥ ሴላ፥ ፋሬስና ዛራሕ ናቸው፤ ዔርና ኦናን ግን በከነዓን ምድር ሞተዋል። የፋሬስ ልጆች ሔጽሮንና ሐሙል ናቸው።
ከዚህ በኋላ ኤልያስ ድምፁን ከፍ በማድረግ “እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! ስለምን በዚህች ባልዋ በሞተባት ሴት ላይ ይህን የመሰለ አሠቃቂ ነገር አደረግህ? እርስዋ እኔን በማስተናገድ ታላቅ ቸርነት አድርጋልኛለች፤ ታዲያ አንተ ስለምን ልጅዋ እንዲሞት አደረግህ?” ሲል ጸለየ።
ይሁዳ ከከነዓናዊት ሚስቱ ከባትሹዓ ዔር፥ ኦናንና ሼላ ተብለው የሚጠሩ ሦስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ የበኲር ልጁ ዔር በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሰው ስለ ነበር እግዚአብሔር በሞት ስለ ቀሠፈው፥
የገዛ ወንዶች ልጆቹንም በሂኖም ሸለቆ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ፤ እርሱም ራሱ ሟርተኛና አስማተኛ ሆኖ፥ ከጠንቋዮችና ከሙታን ጠሪዎች ምክርን ይጠይቅ ነበር፤ በዚህም ሁሉ አድራጎቱ ታላቅ ኃጢአት ስለ ሠራ፥ እግዚአብሔርን አስቈጣ።
አምላክ ሆይ! አንተ ግን ክፉዎችን ወደ ጥልቅ ጒድጓድ ትጥላቸዋለህ፤ እነዚያ ነፍሰ ገዳዮችና ከዳተኞች ግማሽ ዕድሜአቸውን እንኳ አይኖሩም፤ እኔ ግን በአንተ እተማመናለሁ።
አንድ ሰው ሌላውን ሰው ቢበድል፥ እግዚአብሔር በመታደግ ሊያድነው ይችላል፤ ነገር ግን እግዚአብሔርን የሚበድል ሰው ማን ሊያማልደው ይችላል?” ሆኖም እግዚአብሔር ሊያጠፋቸው ቊርጥ ውሳኔ ስላደረገ የዔሊ ልጆች የአባታቸውን ምክር አልሰሙም።