ዘፍጥረት 36:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዓዳ ለዔሳው ኤሊፋዝን ወለደችለት፤ ባሴማትም ረዑኤልን ወለደችለት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዓዳ ለዔሳው ኤልፋዝን ወለደችለት፤ ቤሴሞት ደግሞ ራጉኤልን ወለደችለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዓዳ ለዔሳው ኤልፋዝን ወለደች፥ ባሴማትም ራዑኤልን ወለደች፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሐዳሶ ለእርሱ ኤልፋዝን ወለደች፤ ቤሴሞትም ራጉኤልን ወለደች፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዓዳ ለዔሳው ኤልፋዝን ወለደች ቤሴሞትም ራጉኤልን ወለደች፤ |
የቴማን አገር ሰው የሆነው ኤሊፋዝ፥ የሹሐ አገር ሰው የሆነው ቢልዳድና የናዕማ አገር ሰው የሆነው ጾፋር፥ እነዚህ ሦስቱ የኢዮብ ወዳጆች ነበሩ። እነርሱም በኢዮብ ላይ የደረሰውን ሥቃይ በሰሙ ጊዜ ሐዘናቸውን ሊገልጹለትና ሊያጽናኑት ከየአገራቸው ተጠራርተው በአንድነት ወደ ኢዮብ መጡ።
ሙሴ የምድያማዊውን የራጉኤልን ልጅ፥ ሆባብን “እነሆ፥ እግዚአብሔር ሊሰጠን ቃል ወደገባልን ምድር ለመሄድ ተዘጋጅተናል፤ እግዚአብሔር እስራኤልን እንደሚያበለጽግ ቃል ገብቶልናል፤ ስለዚህ አንተም ከእኛ ጋር አብረህ ሂድ፤ መልካም እናደርግልሃለን” አለው።