ያዕቆብ ራሔልን ለማግባት ሰባት ዓመት አገለገለ፤ ይሁን እንጂ ራሔልን በጣም ይወዳት ስለ ነበር የቈየበት ጊዜ ጥቂት ቀን ብቻ መስሎ ታየው።
ዘፍጥረት 29:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የልያ ሠርግ ሰባት ቀን እስኪሞላው ድረስ ጠብቅ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሰባት ዓመት የምታገለግለኝ ከሆነ ራሔልን እሰጥሃለሁ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን የጫጕላ ሳምንት ፈጽምና ሌላ ሰባት ዓመት የምታገለግለን ከሆነ፣ ታናሺቱን ደግሞ እንሰጥሃለን።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህችንም ሳምንት ፈጽም፥ ሌላ ሰባት ዓመት ደግሞ እኔን ስለምታገለግለኝ አገልግሎት እርሷን ደግሞ እሰጥሃለሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለዚችም ሰባት ዓመት ፈጽም፤ ሌላ ሰባት ዓመት ደግሞ እኔን ስለምታገለግለኝ አገልግሎት እርስዋን ደግሞ እሰጥሃለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህችንም ሳምንት ፈጽም ሌላ ሰባት ዓመት ደግሞ እኔን ስለምታገለግለኝ አገልግሎት እርስዋን ደግሞ እሰጥሃለሁ። |
ያዕቆብ ራሔልን ለማግባት ሰባት ዓመት አገለገለ፤ ይሁን እንጂ ራሔልን በጣም ይወዳት ስለ ነበር የቈየበት ጊዜ ጥቂት ቀን ብቻ መስሎ ታየው።
ከአንተ ጋር የነበርኩበትን ኻያ ዓመት ያሳለፍኩት በዚህ ሁኔታ ነበር፤ ከዚህም ዐሥራ አራቱን ዓመት ያገለገልኩህ ሁለቱን ሴቶች ልጆችህን ለማግኘት ብዬ ነው፤ የቀሩትን ስድስት ዓመቶች ያገለገልኩህ መንጋዎችህን ለማግኘት ብዬ ነው። ይህም ሆኖ ደመወዜን ዐሥር ጊዜ ለዋወጥክብኝ።
ታዲያ እግዚአብሔር እናንተና ሚስቶቻችሁ አንድ አካልና አንድ መንፈስ እንዲኖራችሁ አድርጎ አልነበረምን? በዚህስ የእርሱ ዓላማ ምን ነበር? ዋና ዓላማው የእግዚአብሔር ሕዝቦች የሆኑ ልጆችን እንድትወልዱ በመፈለግ ነበር፤ ስለዚህ ከእናንተ እያንዳንዱ ለሚስቱ የገባውን ቃል ኪዳን አያፍርስ።
ሶምሶንም እንዲህ አላቸው፤ “እስቲ ታውቁ እንደ ሆነ አንድ እንቆቅልሽ ልንገራችሁ፤ በሰባቱ የሠርጉ በዓል ቀኖች ውስጥ ይህን እንቆቅልሽ ፈትታችሁ ብትነግሩኝ፥ ሠላሳ የበፍታ ቀሚስና ሠላሳ ቅያሬ ልብስ እሰጣችኋለሁ፤