ይስሐቅም “ልጄ በል ከአደንከው ሥጋ አቅርብልኝ፤ ከበላሁም በኋላ እመርቅሃለሁ” አለው። ያዕቆብም ምግቡን አቀረበለት፤ የወይን ጠጅም እንዲጠጣ አመጣለት።
ዘፍጥረት 27:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ አባቱ ይስሐቅ “ልጄ ሆይ፥ ቀረብ በልና ሳመኝ” አለው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም አባቱ ይሥሐቅ፣ ያዕቆብን፣ “ልጄ ሆይ፤ እስኪ ቀረብ በልና ሳመኝ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አባቱ ይስሐቅም፦ “ልጄ ሆይ፥ ወደ እኔ ቅረብ ሳመኝም” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አባቱ ይስሐቅም፥ “ልጄ ሆይ፥ ወደ እኔ ቅረብ፤ ሳመኝም” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አባቱ ይስሐቅም ልጄ ሆይ ወደ እኔ ቅረብ ሳመኝም አለው። |
ይስሐቅም “ልጄ በል ከአደንከው ሥጋ አቅርብልኝ፤ ከበላሁም በኋላ እመርቅሃለሁ” አለው። ያዕቆብም ምግቡን አቀረበለት፤ የወይን ጠጅም እንዲጠጣ አመጣለት።
ያዕቆብም ቀርቦ ሳመው። ይስሐቅ የያዕቆብን ልብስ ባሸተተ ጊዜ እንዲህ ሲል መረቀው፥ “እነሆ የልጄ መልካም ሽታ፥ እግዚአብሔር እንደ ባረከው የእርሻ ሽታ ነው፤
ስለዚህም ኢዮአብ ወደ ንጉሥ ዳዊት ሄደና አቤሴሎም ያለውን ሁሉ ነገረው፤ ንጉሡም አቤሴሎምን አስጠራ፤ አቤሴሎምም ሄዶ በንጉሡ ፊት ወደ መሬት ለጥ ብሎ እጅ ነሣ፤ ንጉሡም ሳመው።