አገልጋዩም እንዲህ ብሎ ጸለየ፤ “የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ ዛሬ የእኔን ሐሳብ በመፈጸም ለጌታዬ ለአብርሃም ዘለዓለማዊ ፍቅርህን ግለጥ።
ዘፍጥረት 27:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይስሐቅም “ልጄ ሆይ፥ እንዴት በቶሎ ልታገኝ ቻልክ?” አለው። ያዕቆብም “አምላክህ እግዚአብሔር ስለ ረዳኝ በቶሎ ለማግኘት ቻልኩ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሥሐቅ ልጁን፣ “ልጄ ሆይ፤ ከመቼው ቀንቶህ መጣህ?” ሲል ጠየቀው። ያዕቆብም፣ “እግዚአብሔር አምላክህ አሳካልኝ” ብሎ መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይስሐቅም ልጁን፦ “ልጄ ሆይ፥ እንዴት ፈጥነህ አገኘኸው?” አለው። እርሱም፦ “ጌታ እግዚአብሔር ወደ እኔ ስለ አቀረበው ነው” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይስሐቅም ልጁን፥ “ልጄ ሆይ፥ ፈጥነህ ያገኘኸው ይህ ምንድን ነው?” አለው። እርሱም፥ “አምላክህ እግዚአብሔር በፊቴ የሰጠኝ ነው” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይስሐቅም ልጁን፦ ልጄ ሆይ እንዴት ፈጥነህ አገኘኸው? አለው እርሱም፦ እግዚአብሔር አምላክህ ወደ እኔ ስለ አቀረበው ነው አለ። |
አገልጋዩም እንዲህ ብሎ ጸለየ፤ “የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ ዛሬ የእኔን ሐሳብ በመፈጸም ለጌታዬ ለአብርሃም ዘለዓለማዊ ፍቅርህን ግለጥ።