Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 27:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ይስ​ሐ​ቅም ልጁን፥ “ልጄ ሆይ፥ ፈጥ​ነህ ያገ​ኘ​ኸው ይህ ምን​ድን ነው?” አለው። እር​ሱም፥ “አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፊቴ የሰ​ጠኝ ነው” አለ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ይሥሐቅ ልጁን፣ “ልጄ ሆይ፤ ከመቼው ቀንቶህ መጣህ?” ሲል ጠየቀው። ያዕቆብም፣ “እግዚአብሔር አምላክህ አሳካልኝ” ብሎ መለሰለት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ይስሐቅም ልጁን፦ “ልጄ ሆይ፥ እንዴት ፈጥነህ አገኘኸው?” አለው። እርሱም፦ “ጌታ እግዚአብሔር ወደ እኔ ስለ አቀረበው ነው” አለ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ይስሐቅም “ልጄ ሆይ፥ እንዴት በቶሎ ልታገኝ ቻልክ?” አለው። ያዕቆብም “አምላክህ እግዚአብሔር ስለ ረዳኝ በቶሎ ለማግኘት ቻልኩ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ይስሐቅም ልጁን፦ ልጄ ሆይ እንዴት ፈጥነህ አገኘኸው? አለው እርሱም፦ እግዚአብሔር አምላክህ ወደ እኔ ስለ አቀረበው ነው አለ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 27:20
4 Referencias Cruzadas  

እን​ዲ​ህም አለ፥ “የጌ​ታዬ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ እማ​ል​ድ​ሃ​ለሁ፤ መን​ገ​ዴን ዛሬ በፊቴ አቅ​ና​ልኝ፤ ለጌ​ታ​ዬም ለአ​ብ​ር​ሃም ምሕ​ረ​ትን አድ​ርግ።


ይስ​ሐ​ቅም ያዕ​ቆ​ብን፥ “ልጄ ሆይ፥ አንተ ልጄ ዔሳው እንደ ሆንህ ወይም እን​ዳ​ል​ሆ​ንህ ቅረ​በ​ኝና ልዳ​ስ​ስህ” አለው።


በውኑ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የም​ት​ና​ገሩ አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምን? በፊቱ ሽን​ገ​ላን ታወ​ራ​ላ​ች​ሁን?


“የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የአ​ም​ላ​ክ​ህን ስም በከ​ንቱ አት​ጥራ፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስሙን በከ​ንቱ የሚ​ጠ​ራ​ውን ከበ​ደል አያ​ነ​ጻ​ው​ምና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos