ዘፍጥረት 25:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ያዕቆብ የምስሩን ወጥ በእንጀራ አድርጎ ሰጠው፤ ዔሳውም ከበላና ከጠጣ በኋላ ተነሥቶ ሄደ፤ በዚህ ዐይነት ዔሳው ብኲርናውን በመናቅ አቃለላት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብም ለዔሳው እንጀራና የምስር ወጥ ሰጠው፤ እርሱም ከበላና ከጠጣ በኋላ ተነሥቶ ሄደ። ዔሳው ብኵርናውን እንዲህ አድርጎ አቃለላት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ለዔሳው እንጀራና የምስር ወጥ ሰጠው፤ ዔሳውም ከበላና ከጠጣ በኋላ ተነሥቶ ሄደ፤ በዚህ ዓይነት ዔሳው ብኩርናውን አቃለላት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብም ለዔሳው እንጀራና የምስር ንፍሮ ሰጠው፤ በላ፥ ጠጣ፥ ተነሥቶም ሄደ፤ ዔሳውም ብኵርናውን አቃለላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብም ለዔሳው እንጀራን የምስር ወጥ ሰጠው በላ ጠጣ ተነሥቶም ሄደ፤ እንዲሁም ዔሳው ብኵርናውን አቃለላት። |
በአብርሃም ዘመን ከደረሰው ራብ ሌላ ዳግመኛ ራብ በምድር ላይ መጣ፤ በዚህ ምክንያት ይስሐቅ የፍልስጥኤማውያን ንጉሥ አቤሜሌክ ወዳለበት ወደ ገራር ሄደ፤
ስለዚህ ሰው በዚህ ዓለም ሲኖር የተሰጠው ዕድል ፈንታ መብላት፥ መጠጣትና ራሱን ማስደሰት መሆኑን አረጋገጥኩ፤ እግዚአብሔር በዚህ ዓለም በሰጠው ዘመን፥ ሰው ሁሉ ሠርቶ ያገኘውን ሀብት በዚህ ዐይነት ይደሰትበታል።
እናንተ ግን ጥሪውን በመቀበል ፈንታ በዓል አደረጋችሁ፤ የምትበሉትንም በግና በሬ ዐረዳችሁ፤ ወይን ጠጅም ጠጥታችሁ “ነገ እንሞታለን ዛሬ እንብላ እንጠጣ!” አላችሁ።
እግዚአብሔርም “በቤተ መቅደስ የገንዘብ መቀበያ ሣጥን ውስጥ ጣለው” አለኝ። ስለዚህም ለእኔ “በቂ ደመወዝ ነው” ብለው የሰጡኝን ሠላሳ ብር ወስጄ በሸክላ ሠሪው ገንቦ ውስጥ ጣልኩት።
እንደ ሰው አስተሳሰብ እኔ በኤፌሶን ከአራዊት ጋር መታገሌ ጥቅሜ ምንድን ነው? ሙታን ከሞት የማይነሡ ከሆነማ “ነገ ስለምንሞት ኑ እንብላ፤ እንጠጣ” እንደ ተባለው መሆኑ ነው።