Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 25:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ከዕለታት አንድ ቀን ያዕቆብ ቀይ የምስር ወጥ በመሥራት ላይ እንዳለ ዔሳው ከአደን መጣ፤ በጣም እርቦት ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 አንድ ቀን ያዕቆብ ወጥ እየሠራ ሳለ ዔሳው እጅግ ተርቦ ከዱር መጣ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ከዕለታት አንድ ቀን ያዕቆብ ወጥ ሲሠራ፥ ዔሳው ከአደን መጣ፤ በጣም እርቦት ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ለያ​ዕ​ቆ​ብም የም​ስር ንፍሮ ቀቀ​ለ​ች​ለት፤ ዔሳ​ውም ደክሞ ከበ​ረሃ ገባ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ያዕቆብም ወጥ ሠራ ዔሳውም ደክሞ ከበረሃ ገባ፤

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 25:29
10 Referencias Cruzadas  

ስለዚህም ያዕቆብን “ከዚህ ከቀይ ወጥ ስጠኝ” አለው። ኤዶም የተባለውም በዚህ ምክንያት ነበር።


ከዚህ በኋላ ያዕቆብ የምስሩን ወጥ በእንጀራ አድርጎ ሰጠው፤ ዔሳውም ከበላና ከጠጣ በኋላ ተነሥቶ ሄደ፤ በዚህ ዐይነት ዔሳው ብኲርናውን በመናቅ አቃለላት።


በመላ አገሪቱ ራብ በነበረበት በአንድ ወቅት ኤልሳዕ ወደ ጌልጌላ ተመልሶ መጣ፤ በዚያም የነቢያትን ጉባኤ በማስተማር ላይ ሳለ አገልጋዩን “ትልቅ ድስት ጥደህ ወጥ ሥራላቸው” አለው።


ከነቢያቱም አንዱ ጎመን የሚመስል ቅጠላ ቅጠል ለመልቀም ወደ ሜዳ ሔደ፤ እርሱም በዱር ውስጥ የበቀለ የቅል ሐረግ አገኘ፤ መሸከም የሚችለውን ያኽል በርከት ያለ ቅል ቈርጦ አመጣ፤ የዚያንም ምንነት ሳያውቅ ከትፎ ወጡ ውስጥ ጨመረው፤


እውነተኞች ሊበሉ የሚፈልጉትን ያኽል ያገኛሉ። ኃጢአተኞች ግን ዘወትር ይራባሉ።


ለምሳሌ አንድ ሰው የተቀደሰ ሥጋ ከመሠዊያ ላይ ወስዶ በመጐናጸፊያው ጠቅልሎ ቢይዝ፥ ልብሱም እንጀራና ወጥ፥ የወይን ጠጅና ዘይት ወይም ማናቸውንም ዐይነት ምግብ ቢነካ፥ ምግቡ ሁሉ በዚያ ሰው ምክንያት የተቀደሰ ሊሆን ይችላልን?” በላቸው፤ በዚህ መሠረት ነቢዩ ከጠየቃቸው በኋላ፥ ካህናቱ “የተቀደሰ ሊሆን አይችልም” ሲሉ መለሱ።


ነገር ግን ከወታደሮቹ አንዱ “እኛ ሁላችን በራብ ደክመን ዝለናል፤ አባትህ ግን ‘በዛሬው ዕለት ምንም ዐይነት ምግብ የሚመገብ ሰው የተረገመ ይሁን’ ሲል በብርቱ አስጠንቅቆናል” አለው።


በዚያን ቀን እስራኤላውያን ከሚክማስ እስከ አያሎን ባለው መንገድ ሁሉ እያሳደዱ በመውጋት ፍልስጥኤማውያንን ድል መቱ፤ በዚህም ጊዜ እስራኤላውያንም በራብ እጅግ ዝለው ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos