ገና ጸሎቱን ሳይጨርስ ርብቃ እንስራ ተሸክማ መጣች፤ የዚህችም ልጅ አባት በቱኤል ይባል ነበር፤ እርሱም የአብርሃም ወንድም ናኮር ከሚስቱ ከሚልካ የወለደው ነው።
ዘፍጥረት 24:50 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ላባና ባቱኤልም “ይህ ነገር ከእግዚአብሔር የመጣ ስለ ሆነ፥ መከልከል አንችልም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ላባና ባቱኤል እንዲህ ሲሉ መለሱ፤ “ነገሩ ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ በዚህም ሆነ በዚያ ምንም ማለት አንችልም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ላባና ባቱኤልም መለሱ እንዲህም አሉ፦ “ነገሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ መጥቷል ክፉም በጎም ልንመልስልህ አንችልም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባቱኤልና ላባም መለሱ፤ እንዲህም አሉ፥ “ነገሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ መጥቶአል፤ ክፉ ወይም በጎ ልንመልስልህ አንችልም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ላባና ባቱኤልም መለሱ እንዲህም አሉ፦ ነገሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ መጥቶአል ክፉም በጎ፥ ልንመልስልህ አንችልም |
ገና ጸሎቱን ሳይጨርስ ርብቃ እንስራ ተሸክማ መጣች፤ የዚህችም ልጅ አባት በቱኤል ይባል ነበር፤ እርሱም የአብርሃም ወንድም ናኮር ከሚስቱ ከሚልካ የወለደው ነው።
ከወርቅና ከብር የተሠሩ ጌጣጌጦችን፥ እንዲሁም ልብስ አውጥቶ ለርብቃ ሰጣት፤ ለወንድምዋና ለእናትዋም በጣም ውድ የሆኑ ስጦታዎችን አውጥቶ ሰጣቸው።
ጒዳት ላደርስብህ እችል ነበር፤ ነገር ግን ባለፈው ሌሊት የአባትህ አምላክ ‘ያዕቆብን፥ ክፉም ሆነ ደግ አንድ ቃል እንዳትናገረው’ ብሎ አስጠነቀቀኝ፤
የእኅቱን የትዕማርን ክብረ ንጽሕና በመድፈሩም ምክንያት አቤሴሎም አምኖንን እጅግ ጠላው፤ ዳግመኛም ክፉም ሆነ ደግ ሊያነጋግረው አልፈለገም።
ይህም የሆነበት ምክንያት ከሴሎ በመጣው በነቢዩ አኪያ አማካይነት ስለ ናባጥ ልጅ ስለ ኢዮርብዓም እግዚአብሔር የተናገረው ቃል እንዲፈጸም ነው፤ ንጉሥ ሮብዓምም የሕዝቡን ሐሳብ ችላ በማለት ሳይቀበል የቀረበትም ምክንያት እግዚአብሔር ይህን ለውጥ ለማድረግ ስለ ወሰነ ነው።
“ወንድሞቻችሁ በሆኑት በእስራኤላውያን ላይ አደጋ አትጣሉ፤ ሁላችሁም ወደየቤታችሁ ሂዱ፤ ይህ የሆነው በእኔ ፈቃድ ነው” ብሎ እንዲነግር አዘዘው። እነርሱም ሁሉ ለእግዚአብሔር ቃል ታዛዦች በመሆን ወደየቤታቸው ተመልሰው ሄዱ።
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ “በቅዱሳት መጻሕፍት ‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ ዋና የማእዘን ራስ ሆነ፤ ይህም የጌታ ሥራ ነው፤ ለዐይኖቻችንም ድንቅ ነው፤’ ተብሎ የተጻፈውን ከቶ አላነበባችሁምን?
እኛ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ባመንን ጊዜ እግዚአብሔር ለእኛ የሰጠውን ስጦታ ለእነርሱም ከሰጣቸው፤ ታዲያ፥ እግዚአብሔርን ለመከልከል የምችል እኔ ማን ነኝ!”