ዘፍጥረት 24:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጅትዋ ወደ ቤት ሮጣ ሄደችና የሆነውን ሁሉ ለእናትዋና ከእርስዋ ጋር ላሉት ሁሉ ነገረቻቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጅቷ ሮጣ ሄዳ፣ የሆነውን ሁሉ ለእናቷ ቤተ ሰቦች ነገረች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብላቴናይቱም ሮጠች፥ ለእናትዋም ቤት ይህን ነገር ሁሉ ተናገረች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብላቴናዪቱም ሮጠች፥ ለእናቷም ቤት ይህን ሁሉ ነገር ተናገረች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብላቴናይቱም ሮጠች ለእናትዋም ቤት ይህን ነገር ሁሉ ተናገርች |
ከዚህ በኋላ ለጌታዬ ልጅ ሚስት የምትሆነዋን ሴት ወዳገኘሁበት ወደ ጌታዬ ወንድም ቤት በቀና መንገድ ለመራኝ ለእግዚአብሔር በጒልበቴ ተንበርክኬ ሰገድሁ፤ የጌታዬን የአብርሃምን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገንኩ፤
ከዚህ በኋላ ይስሐቅ እናቱ ሣራ ትኖርበት ወደነበረው ድንኳን ርብቃን ይዞአት ገባ፤ ሚስትም ሆነችው፤ ይስሐቅ ርብቃን ወደዳት፤ በእናቱ ሞት ምክንያት ከደረሰበትም ሐዘን በዚህ ሁኔታ ተጽናና።
ከዚህ በኋላ ላባ ወደ ያዕቆብ ወደ ልያና ወደ ሁለቱ አገልጋዮች ድንኳን ተራ በተራ ገብቶ በረበረ፤ ነገር ግን ምንም አላገኘም፤ በመጨረሻ ወደ ራሔል ድንኳን ገባ፤