ዘፍጥረት 22:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን የእግዚአብሔር መልአክ ከሰማይ “አብርሃም! አብርሃም!” ብሎ ጠራው። አብርሃምም “እነሆ፥ አለሁኝ!” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር መልአክ ግን ከሰማይ፣ “አብርሃም! አብርሃም!” ብሎ ጠራው። አብርሃምም፣ “እነሆ፤ አለሁ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን የጌታ መልአክ “አብርሃም! አብርሃም!” ሲል ከሰማይ ተጣራ። አብርሃምም “እነሆ፥ አለሁኝ!” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር መልአክም ከሰማይ ጠራና፥ “አብርሃም! አብርሃም” አለው፤ እርሱም፥ “እነሆኝ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔር መልአክም ከሰማይ ጠራና፦ አብርሃም አብርሃም አለው፤ |
እግዚአብሔርም ልጁ ምርር ብሎ ሲያለቅስ ሰማ፤ የእግዚአብሔርም መልአክ ከሰማይ አጋርን “አጋር ሆይ፤ የምትጨነቂበት ነገር ምንድን ነው? እግዚአብሔር የልጁን ለቅሶ ሰምቶአልና አይዞሽ አትፍሪ፤
ከዚህ ሁሉ ነገር በኋላ እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው፤ እግዚአብሔርም “አብርሃም!” ብሎ ጠራው፤ አብርሃምም “እነሆ፥ አለሁኝ!” ብሎ መለሰ።
መልአኩም “ልጁን አትንካ፤ ምንም ዐይነት ጒዳት አታድርስበት፤ አንድ ልጅህን እንኳ ለእኔ ከመስጠት ስለ አልተቈጠብክ እነሆ፥ እኔን እግዚአብሔርን የምትፈራ መሆንህን ተረድቼአለሁ።”
ከአባቴ ቤትና ከትውልድ አገሬ አውጥቶ ይህን ምድር ለዘሬ እንደሚሰጥ በመሐላ ቃል የገባልኝ እግዚአብሔር፥ የሰማይ አምላክ ከዚያ ለልጄ ሚስት ማግኘት እንድትችል መልአኩን በፊትህ ይልካል።
እስራኤልም ዮሴፍን “እነሆ፥ ወንድሞችህ መንጋውን ይዘው ወደ ሴኬም መሰማራታቸውን ታውቃለህ፤ ስለዚህ ወደ እነርሱ ልልክህ እፈልጋለሁ” አለው። ዮሴፍም “እሺ እሄዳለሁ” አለ።
እኔን ከጒዳት ሁሉ ያዳነኝ መልአክ እነርሱንም ይጠብቃቸው። የእኔ ስም፥ የአባቶቼም የአብርሃምና የይስሐቅ ስም በነዚህ ልጆች ሲታወስ ይኑር፤ ዘራቸውም በምድር ላይ ይብዛ።”
እዚያም የእግዚአብሔር መልአክ በቊጥቋጦ ውስጥ በተቀጣጠለ የእሳት ነበልባል መካከል ሆኖ ተገለጠለት፤ ሙሴም ቊጥቋጦው በእሳት ተያይዞ ሳለ ምንም አለመቃጠሉን ተመለከተና፥
ሙሴም ሁኔታውን ለማየት በቀረበ ጊዜ እግዚአብሔር ተመለከተው፤ በቊጥቋጦውም መካከል ሆኖ “ሙሴ! ሙሴ!” ብሎ ጠራው። ሙሴም “እነሆ፥ አለሁ” አለ።
ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር “ማንን እልካለሁ? መልእክተኛ የሚሆንልንስ ማን ነው?” ሲል ሰማሁት፤ እኔም “እነሆ እኔ እሄዳለሁ! እኔን ላከኝ!” አልኩ።
ሁላችንም በመሬት ላይ ወድቀን ሳለ በአይሁድ ቋንቋ ‘ሳውል! ሳውል! ስለምን ታሳድደኛለህ? በሰይፍ ስለት ላይ ብትቆም ራስህን ትጐዳለህ’ የሚል ድምፅ ሰማሁ።
የእግዚአብሔር መልአክ ከጌልጌላ ወደ ቦኪም ሄዶ እስራኤላውያንን እንዲህ አላቸው፤ “እኔ ከግብጽ ምድር አውጥቼ ለቀድሞ አባቶቻችሁ ልሰጣቸው ቃል ወደገባሁላቸው ምድር አመጣኋችሁ፤ እንዲህም አልኩ፦ ‘ከእናንተ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን ከቶ አላፈርስም፤
እግዚአብሔርም መጥቶ በዚያ ቆመ፤ ከዚያም በፊት ያደርግ በነበረው ዐይነት “ሳሙኤል! ሳሙኤል!” ብሎ ጠራው። ሳሙኤልም “ጌታ ሆይ! እነሆ አገልጋይህ እሰማለሁና ተናገር” አለው።