ዘፍጥረት 21:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ግብጻዊትዋ አጋር ለአብርሃም የወለደችለት እስማኤል ከዕለታት አንድ ቀን ሣራ ከልጅዋ ከይስሐቅ ጋር ሲጫወት አየችው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሌላ በኩል ደግሞ፣ ግብጻዊቷ አጋር ለአብርሃም የወለደችለት እስማኤል በይሥሐቅ ላይ ሲያሾፍበት ሣራ አየች፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሣራም ግብፃዊቱ አጋር ለአብርሃም የወለደችለትን ልጅ ሲስቅ አየችው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሣራም ግብፃዊቱ አጋር ለአብርሃም የወለደችለትን ልጅ ይስማኤልን ከልጅዋ ከይስሐቅ ጋር ሲጫወት አየችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሣራም ግብፃዊቱ አጋር ለአብርሃም የወለደችለትን ልጅ ሲስቅ አየችው። |
ስለ እስማኤል ያቀረብከውንም ልመና ሰምቼአለሁ፤ እርሱንም እባርከዋለሁ፤ ብዙ ልጆችን እሰጠዋለሁ፤ ዘሩንም እጅግ አበዛዋለሁ፤ እርሱ የዐሥራ ሁለት መሳፍንት አባት ይሆናል፤ ዘሩንም ታላቅ ሕዝብ አደርገዋለሁ።
መልእክተኞቹ በኤፍሬምና በምናሴ ነገዶች ግዛት ወደሚገኙ ከተማዎች ሁሉ በመሄድ እስከ ዛብሎን ነገድ ሰሜናዊ ግዛት ድረስ ዘለቁ፤ እነዚያ ግን በንቀት እየሳቁ ተሳለቁባቸው፤
እስራኤላውያን ግን በእግዚአብሔር መልእክተኞች ላይ ተሳለቁ፤ በነቢያቱም በማፌዝ፥ የእግዚአብሔርን ቃል አቃለሉ፤ ከዚህም የተነሣ፥ የእግዚአብሔር ቊጣ በሕዝቡ ላይ ወረደ፤ ከታላቅ ቊጣውም ለማምለጥ አልቻሉም።
“አሁን ግን በዕድሜ ከእኔ ያነሱ ሰዎች ያፌዙብኛል፤ የእነርሱ አባቶች የበጎቼን መንጋ ከሚጠብቁ ውሾቼ ጋር እንኳ እንዲሰማሩ የምንቃቸው ሰዎች ነበሩ።
የኢየሩሳሌም ሕዝብ በቀድሞ ጊዜ የነበሩአቸውን የከበሩ ነገሮች በችግራቸውና በጭንቀታቸው ቀን ያስታውሳሉ፤ እነርሱም በጠላት እጅ በወደቁ ጊዜ፥ አንድም ረዳት ባልነበራቸው ጊዜ፥ ጠላቶቻቸው የከተማቸውን ውድቀት ተመልክተው ተሳለቁባቸው።
በቅዱሳት መጻሕፍት “አብርሃም ሁለት ልጆች ነበሩት፤ አንደኛው የተወለደው ከአገልጋይቱ ሴት ሲሆን ሌላው የተወለደው ከነጻይቱ ሴት ነበር” ተብሎ ተጽፎአል።