ነገር ግን ያልተገረዘ ማንም ሰው አይብላ፤ የውጪ አገር ሰው በመካከላችሁ ቢኖርና የእግዚአብሔርን የፋሲካ በዓል ማክበር ቢፈልግ፥ አስቀድማችሁ በቤተሰቡ ያሉትን ወንዶች ሁሉ ግረዙ፤ ከዚያም በኋላ የሀገር ተወላጅ እስራኤላዊ እንደ ሆነ ተቈጥሮ የፋሲካን በዓል ለማክበር ከእናንተ ጋር ይተባበር።
ዘፍጥረት 21:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይስሐቅ ከተወለደ ከስምንት ቀን በኋላ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት አብርሃም ገረዘው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አብርሃም፣ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ልጁን ይሥሐቅን በተወለደ በስምንተኛው ቀን ገረዘው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብርሃምም ልጁን ይስሐቅን እግዚአብሔር እንዳዘዘው በስምንተኛ ቀን ገረዘው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብርሃምም ልጁን ይስሐቅን እግዚአብሔር እንዳዘዘው በስምንተኛው ቀን ገረዘው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብርሃምም ልጁን ይስሐቅን እግዚአብሔር እንዳዘዘው በስምንተኛ ቀን ገረዘው። |
ነገር ግን ያልተገረዘ ማንም ሰው አይብላ፤ የውጪ አገር ሰው በመካከላችሁ ቢኖርና የእግዚአብሔርን የፋሲካ በዓል ማክበር ቢፈልግ፥ አስቀድማችሁ በቤተሰቡ ያሉትን ወንዶች ሁሉ ግረዙ፤ ከዚያም በኋላ የሀገር ተወላጅ እስራኤላዊ እንደ ሆነ ተቈጥሮ የፋሲካን በዓል ለማክበር ከእናንተ ጋር ይተባበር።
ሕፃኑ በተወለደ በስምንተኛው ቀን፥ በግዝረቱ ሥነ ሥርዓት ላይ ለመገኘት ጐረቤቶችዋና ዘመዶችዋ ተሰብስበው መጡ፤ ባባቱ ስም ዘካርያስ ብለው ሊጠሩት ፈልገው ነበር፤
ከስምንት ቀን በኋላ ሕፃኑ በሚገረዝበት ሥነ ሥርዓት ላይ፥ ስሙ “ኢየሱስ” ተብሎ ተጠራ። ይህም ገና ከመፀነሱ በፊት መልአኩ ያወጣለት ስም ነው።
የመገረዝንም ኪዳን ሰጠው፤ ስለዚህ አብርሃም ይስሐቅን በወለደ ጊዜ በስምንተኛው ቀን ገረዘው፤ እንዲሁም ይስሐቅ ልጁን ያዕቆብን ገረዘው። ያዕቆብም የነገድ አባቶች የሆኑትን ዐሥራ ሁለቱን ልጆቹን ገረዘ።