በማግስቱ ጠዋት አብርሃም በማለዳ ተነሣ፤ ጥቂት ምግብ፥ ውሃም በአቁማዳ ሞልቶ ለአጋር ሰጣት፤ ልጁንም በጀርባዋ አሳዝሎ ከቤት አስወጣት፤ እርስዋም ከዚያ ወጥታ በቤርሳቤህ በረሓ ትንከራተት ጀመር።
ዘፍጥረት 21:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁለቱ ተማምለው የተስማሙበት ስፍራ በመሆኑ የዚያ ቦታ ስም ቤርሳቤህ ተባለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ቦታው፣ ሁለቱ ተማምለው የተስማሙበት ስፍራ በመሆኑ ቤርሳቤህ ተባለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ የዚያን ስፍራ ስም ቤርሳቤህ ብሎ ጠራው፥ ከዚያ ሁለቱ ተማምለዋልና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህም ያን ጕድጓድ ዐዘቅተ መሐላ ብሎ ጠራው፤ በዚያ እርስ በርሳቸው ተማምለዋልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ የዚያን ስፍራ ስም ቤርሳቤህ ብሎ ጠራው፤ ከዚያ ሁለቱ ተማምልዋልና። |
በማግስቱ ጠዋት አብርሃም በማለዳ ተነሣ፤ ጥቂት ምግብ፥ ውሃም በአቁማዳ ሞልቶ ለአጋር ሰጣት፤ ልጁንም በጀርባዋ አሳዝሎ ከቤት አስወጣት፤ እርስዋም ከዚያ ወጥታ በቤርሳቤህ በረሓ ትንከራተት ጀመር።
ስለዚህ እኔ የምመክርህ፥ ከአገሪቱ አራት ማእዘኖች ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ያሉትንና ብዛታቸው እንደ ባሕር ዳር አሸዋ የሆነው እስራኤላውያን ሁሉ በአንድነት ሰብስበህ አንተው ራስህ አዛዥ በመሆን ወደ ጦርነቱ እንድትመራቸው ነው።
ቀጥሎም በደቡብ በኩል ወደተመሸገችው ወደ ጢሮስ ከተማና እንዲሁም ወደ ሒዋውያንና ወደ ከነዓናውያን ከተሞች ሁሉ ሄዱ፤ በመጨረሻም በይሁዳ ወደምትገኘው ወደ ቤርሳቤህ ዘለቁ፤
በኖረበትም ዘመን ሁሉ ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ድረስ መላው የይሁዳና የእስራኤል ሕዝብ ያለስጋት በሰላም ይኖር ነበር፤ እያንዳንዱ ቤተሰብ የራሱ የሆነ የወይን ተክልና የበለስ ዛፍ ስለ ነበረው በእነዚህ ተክሎች ጥላ ሥር ያርፍ ነበር።
ወደ ቤርሳቤህ አትሂዱ፤ ቤቴል ፈራርሳ እንዳልነበረች ስለምትሆን በጌልገላ የሚኖሩ ሕዝቦችም ስደት ስለ ተፈረደባቸው ወደ ቤቴልም ሆነ ወደ ጌልጌላ አትሂዱ።”
ከሰሜን እስከ ደቡብ፥ ማለትም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ እንዲሁም በስተምሥራቅ በገለዓድ ምድር ያሉት የእስራኤል ሕዝብ በሙሉ ለጦርነት ተዘጋጁ፤ በአንድነትም ሆነው በምጽጳ በእግዚአብሔር ፊት ተሰበሰቡ፤