ሎጥ ዙሪያውን በተመለከተ ጊዜ የዮርዳኖስ ሸለቆ እስከ ጾዓር ድረስ እንደ እግዚአብሔር ገነት ወይም እንደ ግብጽ ምድር ውሃ የሞላበት መሆኑን አየ፤ ይህን የተመለከተው እግዚአብሔር የሰዶምንና የገሞራን ከተሞች ከማጥፋቱ በፊት ነበር።
ዘፍጥረት 19:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሎጥ በጾዓር መቀመጥ ስለ ፈራ እርሱና ሁለቱ ሴቶች ልጆቹ ወደ ተራራዎቹ ወጥተው መኖሪያቸውን በዋሻ ውስጥ አደረጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሎጥ በዞዓር መኖርን ስለ ፈራ፣ ከዚያ ተነሥቶ ከሁለቱ ሴት ልጆቹ ጋራ በአቅራቢያው ወደሚገኙት ተራሮች ሄደ፤ መኖሪያውንም ከሁለት ሴት ልጆቹ ጋራ በዋሻ ውስጥ አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሎጥም ከዞዓር ወጣ፥ በዞዓር ይቀመጥ ዘንድ ስለ ፈራም ከሁለቱ ሴቶች ልጆቹ ጋር በተራራ ተቀመጠ፥ በዋሻም ከሁለቱ ሴቶች ልጆቹ ጋር ተቀመጠ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሎጥም ከሴጎር ወጣ፤ ከሁለቱም ሴቶች ልጆቹ ጋር በተራራ ተቀመጠ፤ በሴጎር መቀመጥን ፈርቶአልና እርሱና ሁለቱ ሴቶች ልጆቹ በዋሻ ተቀመጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሎጥም ከዞዓር ወጣ በዞዓር ይቀመጥ ዘንድ ስል ፈራም ከሁለቱ ሴቶች ልጆቹ ጋር በተራራ ተቀመጠ። |
ሎጥ ዙሪያውን በተመለከተ ጊዜ የዮርዳኖስ ሸለቆ እስከ ጾዓር ድረስ እንደ እግዚአብሔር ገነት ወይም እንደ ግብጽ ምድር ውሃ የሞላበት መሆኑን አየ፤ ይህን የተመለከተው እግዚአብሔር የሰዶምንና የገሞራን ከተሞች ከማጥፋቱ በፊት ነበር።
ካወጡአቸውም በኋላ ከመላእክቱ አንዱ “ሕይወታችሁን አድኑ! ወደ ኋላ አትመልከቱ! በሸለቆው ውስጥ አትዘግዩ፤ እንዳትሞቱ ወደ ተራራው ሽሹ!” አላቸው።
እኔ አገልጋያችሁ በፊታችሁ ሞገስ ስላገኘሁ ሕይወቴን ለማዳን ታላቅ ርዳታ አድርጋችሁልኛል፤ ነገር ግን ይህ ጥፋት ደርሶብኝ እሞታለሁ ብዬ ስለምሰጋ ወደዚያ ተራራ መሸሽ አልችልም።
ይሁን እንጂ እንደ ውሃ የምትዋልል ስለ ሆንክ፥ የበላይ አለቅነት ለአንተ አይገባም፤ ወደ አባትህ አልጋ ወጥተሃል፤ የአባትህንም ቁባት ደፍረሃል።
ስለ ሞአብ ከልቤ አለቅሳለሁ፤ ሕዝቡ ወደ ጾዓርና ወደ ዔግላት ሸሊሺያ ኰበለሉ፤ ጥቂቶችም ወደ ሉሒት አቀበት ወጡ፤ በሚወጡበትም ጊዜ ያለቅሱ ነበር፤ ሌሎች ደግሞ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ስለ ጥፋታቸው እያለቀሱ ወደ ሖሮናይም ለማምለጥ ይሞክራሉ።
“የሐሴቦንና የዔልዓሌ ሕዝብ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ይጮኻሉ፤ ጩኸታቸውም እስከ ያሀጽ ተሰምቶአል፤ ከጾዓር እስከ ሖሮናይምና ዔግላት ሺሊሺያ ድረስ ተሰምቶአል፤ የኒምሪም ውሃ እንኳ ደርቆአል።