እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “እንዲህስ አይሆንም፤ ነገር ግን ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ይስሐቅ ትለዋለህ፤ ቃል ኪዳኔን ከእርሱና ከዘሩ ጋር ለዘለዓለም አጸናለሁ፤
ዘፍጥረት 17:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን የዛሬ ዓመት በዚህ ጊዜ ከሣራ ከሚወለደው ልጅህ ከይስሐቅ ጋር ቃል ኪዳኔን አጸናለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኪዳኔን ግን የዛሬ ዓመት በዚሁ ጊዜ ሣራ ከምትወልድልህ ልጅ፣ ከይሥሐቅ ጋራ አደርጋለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቃል ኪዳኔን ግን በሚመጣው ዓመት በዚሁ ጊዜ ሣራ ከምትወልድልህ ከይስሐቅ ጋር አቆማለሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቃል ኪዳኔን ግን በሚመጣው ዓመት በዚሁ ጊዜ ሣራ ከምትወልድልህ ከይስሐቅ ጋር አቆማለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቃለ ኪዳኔን ግን በሚመጣው ዓመት በዚሁ ጊዜ ሣራ ከምትወልድልህ ከይስሐቅ ጋር አቆማለሁ። |
እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “እንዲህስ አይሆንም፤ ነገር ግን ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ይስሐቅ ትለዋለህ፤ ቃል ኪዳኔን ከእርሱና ከዘሩ ጋር ለዘለዓለም አጸናለሁ፤
ከሦስቱም እንግዶች አንዱ አብርሃምን “የዛሬ ዓመት በዚህ ጊዜ ተመልሼ እመጣለሁ፤ በዚያን ጊዜ ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅ ትወልዳለች” አለው። እርሱም ይህን በሚናገርበት ጊዜ ሣራ በስተኋላው በድንኳኑ ደጃፍ ቆማ ታዳምጥ ነበር፤
ከቶ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን? እንደ ነገርኩህ የዛሬ ዓመት በዚህ ጊዜ ተመልሼ እመጣለሁ፤ በዚያን ጊዜ ሣራ ወንድ ልጅ ትወልዳለች” አለው።
ከዚህ በኋላ ዮሴፍን እንዲህ ሲል ባረከው፦ “አባቶቼ አብርሃምና ይስሐቅ መንገዱን በመከተል ያገለገሉትና እኔንም ሕይወቴን ሙሉ እስከ ዛሬ ድረስ እረኛ ሆኖ የጠበቀኝ አምላክ እነዚህን ልጆች ይባርክ!
እኔ የቀድሞ አባቶችህ የአብርሃም፥ የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ ነኝ፤” በዚህ ጊዜ ሙሴ እግዚአብሔርን ፊት ለፊት ማየት ስለ ፈራ ፊቱን ሸፈነ።