ከዚህም የተነሣ በአብራም እረኞችና በሎጥ እረኞች መካከል ጠብ ተነሣ፤ በዚያን ዘመን የዚያች ምድር ነዋሪዎች ከነዓናውያንና ፈሪዛውያን ነበሩ።
ዘፍጥረት 15:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአሞራውያንን፥ የከነዓናውያንን፥ የጌርጌሳውያንን፥ የኢያቡሳውያንን ምድር እሰጣለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአሞራውያንን፣ የከነዓናውያንን፣ የጌርጌሳውያንንና የኢያቡሳውያንን ምድር ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፌርዛውያንንም ራፋይምንም አሞራውያንንም ከነዓናውያንንም ጌርጌሳውያንንም ኢያቡሳውያንንም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሞሬዎናውያንንም፥ ከናኔዎናውያንንም፥ ጌርጌሴዎናውያንንም፥ ኢያቡሴዎናውያንንም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፌርዛውያንንም፥ ራፋይምንም፥ አሞራውያንንም፥ ከነዓናውያንንም ጌርጌሳውያንንም፥ ኢያቡሳውያንንም። |
ከዚህም የተነሣ በአብራም እረኞችና በሎጥ እረኞች መካከል ጠብ ተነሣ፤ በዚያን ዘመን የዚያች ምድር ነዋሪዎች ከነዓናውያንና ፈሪዛውያን ነበሩ።
በግፍ ጭቈና ከሚሠቃዩባት ከግብጽ ምድር አውጥቼ እነሆ ዛሬ፥ ከነዓናውያን፥ ሒታውያን፥ አሞራውያን፥ ፈሪዛውያን፥ ሒዋውያንና ኢያቡሳውያን የሚኖሩባትን፥ በማርና በወተት የበለጸገች ሰፊና ለም የሆነች ምድር ልሰጣቸው ቃል ገብቻለሁ።
እነርሱንም ከግብጻውያን እጅ ለማዳን ወርጃለሁ፤ ከግብጽም አውጥቼ አሁን ከነዓናውያን፥ ሒታውያን፥ አሞራውያን፥ ፈሪዛውያን፥ ሒዋውያንና ኢያቡሳውያን፥ የሚኖሩባትን፥ በማርና በወተት የበለጸገችውን ሰፊና ለም የሆነችውን ምድር እሰጣቸዋለሁ።
ፊት ፊትህ እየሄደ የሚመራህ መልአክ እልካለሁ፤ ከነዓናውያንን፥ አሞራውያንን፥ ሒታውያንን፥ ፈሪዛውያንን፥ ሒዋውያንንና ኢያቡሳውያንን ከፊትህ አባርራለሁ።
ዛሬ ለእናንተ የምሰጠውን ሕግ ጠብቁ፤ እኔም አሞራውያንን፥ ከነዓናውያንን፥ ሒታውያንን፥ ፈሪዛውያንን፥ ሒዋውያንንና ኢያቡሳውያንን ከፊታችሁ አባርራለሁ፤
ዐማሌቃውያን በኔጌብ ምድር የሚኖሩ ሲሆን፥ ሒታውያን፥ ኢያቡሳውያንና አሞራውያን በተራራማው አገር፥ ከነዓናውያን ደግሞ በዮርዳኖስ ወንዝ ዳርና በሜዲቴራኒያን በባሕር ዳር ይኖራሉ።”
ሙሴም ያዕዜርን የሚሰልሉ ሰዎች ላከ፤ እስራኤላውያንም ከተማይቱንና በዙሪያዋ ያሉትን ታናናሽ ከተሞች ያዙ፤ በዚያም ይኖሩ የነበሩትን አሞራውያን አባረሩ።
ኢየሱስ የገሊላን ባሕር ተሻግሮ፥ ወደ ጌርጌሴኖን አገር በመጣ ጊዜ፥ አጋንንት የያዛቸው ሁለት ሰዎች ከመቃብር ቦታ ወጥተው ተገናኙት፤ በጣምም አደገኞች ስለ ነበሩ ማንም ሰው በዚያ መንገድ ማለፍ አይችልም ነበር።
ስለዚህም በሒታውያን፥ በአሞራውያን፥ በከነዓናውያን፥ በፈሪዛውያን፥ በሒዋውያንና በኢያቡሳውያን ላይ እግዚአብሔር ባዘዛችሁ መሠረት ሕዝቡን በሙሉ ደምስሱ፤
“እግዚአብሔር አምላክህ ልትወርሳት ወደምትገባባት ምድር በሚያመጣህ ጊዜ በፊትህ ያሉትን ብዙ ሕዝቦች ያስወግድልሃል፤ እነርሱም ከአንተ በብዛትና በኀይል የሚበልጡት ሰባት የአሕዛብ ነገዶች ሒታውያን፥ ጌርጌሳውያን፥ አሞራውያን፥ ከነዓናውያን፥ ፈሪዛውያን፥ ሒዋውያንና ኢያቡሳውያን ተብለው የሚጠሩት ናቸው።
ኢያሱም ንግግሩን በመቀጠል፦ “ሕያው እግዚአብሔር በመካከላችሁ መሆኑን የምታውቁት እናንተ ወደ ፊት እየገፋችሁ በሄዳችሁ መጠን እርሱ ከነዓናውያንን፥ ሒታውያንን፥ ሒዋውያንን፥ ፈሪዛውያንን፥ ጌርጌሳውያንን፥ አሞራውያንንና ኢያቡሳውያንን ከፊታችሁ የሚያስወጣ በመሆኑ ነው።