ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “እነሆ፥ እኔ የምሞትበት ጊዜ ተቃርቦአል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው፤ ወደ ቀድሞ አባቶቻችሁም ምድር ይመልሳችኋል፤
ዘፍጥረት 15:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በባርነት የሚገዛቸውን ሕዝብ እቀጣለሁ፤ ከዚያም በኋላ ብዙ ሀብት ይዘው ከዚያ አገር ይወጣሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን በባርነት የሚገዛቸውን ሕዝብ እቀጣዋለሁ፤ ከዚያም ብዙ ሀብት ይዘው ይወጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞም በባርነት በሚገዙአቸው ሕዝብ ላይ እኔ እፈርዳለሁ፥ ከዚያም በኋላ በብዙ ከብት ይወጣሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም የሚያሠቃዩአቸውን እኔ እፈርድባቸዋለሁ። ከዚህም በኋላ ከብዙ ገንዘብ ጋር ወደዚህ ይወጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም በባርነት በገዙአቸው ሕዝብ ላይ እኔ እፈርዳለሁ ከዚያም በኍላ በብዙ ከብት ይወጣሉ። |
ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “እነሆ፥ እኔ የምሞትበት ጊዜ ተቃርቦአል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው፤ ወደ ቀድሞ አባቶቻችሁም ምድር ይመልሳችኋል፤
ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ወንድሞቹን እንዲህ አላቸው፤ “እነሆ እኔ የምሞትበት ጊዜ ተቃርቦአል፤ እናንተን ግን እግዚአብሔር በረድኤት ይጐበኛችኋል፤ ከዚህም አገር አውጥቶ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ለመስጠት በመሐላ ቃል ወደ ገባላቸው ምድር ይመልሳችኋል።
እኔ ያመፅኩት በአንተ ላይ ነው፤ የበደልኩትም አንተን ብቻ ነው፤ አንተ የምትጠላውን ነገር አደረግሁ፤ ስለዚህ በእኔ ላይ መፍረድህና እኔንም መቅጣትህ ትክክል ነው።
እኩለ ሌሊት ሲሆን እግዚአብሔር ከንጉሡ አልጋ ወራሽ ጀምሮ ከምድር በታች ባለ እስር ቤት ውስጥ እስከ ተጣለው የእስረኛ ልጅ ድረስ በግብጽ ምድር በኲር የሆነውን ወንድ ልጅ ሁሉ በሞት ቀጣ፤ በኲር ሆነው የተወለዱ እንስሶችም ተገደሉ።
ቀጥሎም ‘ባሪያ አድርጎ በሚገዛው ሕዝብ ላይ እፈርድበታለሁ፤ ከዚያም በኋላ ነጻ ወጥተው በዚህ ስፍራ ያመልኩኛል’ ብሎ እግዚአብሔር ተናግሮአል።
እናንተ ግን እሳት እንደሚነድበት የብረት ምድጃ ከሆነችው ከግብጽ መንጥቆ እግዚአብሔር ያወጣችሁ ዛሬ እንደ ሆናችሁት ሁሉ ለራሱ የተለያችሁ ወገኖቹ እንድትሆኑ ነው።
አምላካችን እግዚአብሔር አባቶቻችንንና እኛን ከግብጽ ባርነት አውጥቶናል፤ ያደረገውን ተአምራት ሁሉ አይተናል፤ ሕዝቦችን ሁሉ አልፈን በመጣንበት ጊዜ በሰላም ጠብቆናል፤
ያዕቆብና ቤተሰቡ ወደ ግብጽ ወርደው በዚያ ሲኖሩ ግብጻውያን የጭቈና ቀንበር ጫኑባቸው፤ የቀድሞ አባቶቻቸውም ርዳታ ለማግኘት ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን ላከላቸው፤ እነርሱም ከግብጽ መርተው በማውጣት በዚህች ምድር እንዲሰፍሩ አደረጉአቸው፤